ጥር 17 2017 - የኢትዮጵያ ከሶስት ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጥ ልትጀምር ነው
- sheger1021fm
- Jan 25
- 1 min read
የኢትዮጵያ ከሶስት ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጥ ልትጀምር ነው፡፡
በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ለታንዛኒያ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መሸጥ ትጀምራለች ተብሏል፡፡
ይህን የሚያስችለወን ስምምነት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የታንዛኒያ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ኩባንያ እና የኬንያ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኩባንያ የሦስትዮሽ የኃይል ሽያጭ ድርድር ስምምነት ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ስምምነቱ በኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ላይ ያተኮሩ የህግ፣ የኮሜርሻል እና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ መሠረት ያደረገ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ስመነቱም ከታንዛኒያ ጋር የኃይል ሽያጭ እንዲሁም ኬንያ ከታንዛንያ ጋር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የኪራይ ውል ሥምምነት መሆኑንን የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሃይል ተናግሯል።
የሦስትዮሽ ሥምምነቱ ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችላትን መብት የሚሰጣት መሆኑንም ተጠቅሷል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs











Comments