top of page

ግንቦት 6 2017 - ግሎባል ቁጠባና ብድር የተመሠረተበትን ዘጠነኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ወር የሚቆይ አዲስ ፓኬጅ ማዘጋጀቱን ተናገረjust now

  • sheger1021fm
  • 5 hours ago
  • 1 min read

ግሎባል ቁጠባና ብድር የተባለው ተቋም የተመሠረተበትን ዘጠነኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ወር የሚቆይ አዲስ ፓኬጅ ማዘጋጀቱን ተናገረ፡፡


ድርጅቱ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው ባለው ፓኬጅ የንብረቱን ዋጋ 60 በመቶ ብቻ በመቆጠብ የንብረት ባለቤት ለማድረግ ተዘጋጅታለሁ ብሏል፡፡


የድርጅቱ የኦፕሬሽን ሃላፊ አቶ ብሩክ ፀጋዬ እንደነገሩን ከዚህ ቀደም በ30 በመቶ ቁጠባ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ይሰጡት የነበረውን የብድር አገልግሎት በአዲሱ ፓኬጅ በተዘጋጀው የተሸከርካሪ ብድር የተሸከርካሪውን ዋጋ 60 በመቶውን መቆጠብ ለሚችል ማንኛው ሰው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተሸከርካሪውን ማቅረብ እንደሚችሉ ነግረውናል፡፡


አሁን ከጀመረው አዲስ ፓኬጅ በተጨማሪ በመደበኛነት እስከ 30 በመቶ ለሚቆጥብ የተቋሙ አባል የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥ የሚናገሩት አቶ ብሩክ፤ የቤቱን ዋጋ እስከ 30 በመቶ ድረስ ለቆጠበ አባል እስከ 10 ሚሊዮን ብር የደረሰ የቤት ብድር እንደሚሰጡ እንዲሁም በዚህ መንገድ የህክምናና የትምህርት ብድር እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡


ከሌሎች መሰል የብድርና ቁጠባ ተቋማት የሚለየኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈለገውን ብድር ስለማቀርብ ነው የሚለው ግሎባል ቁጠባና ብድር በተለይ ለሴቶችና ለወጣቶች እስከ 13 በመቶ በደረሰ ወለድ እንደሚያበድር የድርጅቱ የኦፕሬሽን ሃላፊ አቶ ብሩክ ፀጋዬ አብራርተዋል፡፡


ባለፈው አንድ ዓመት 180 ብድሮችን ለአባላቱ መስጠቱ ሃላፊው ነግረውናል፤ከዚህም ውስጥ 110 መኪኖችን፣70 የቤት፣የስራ ማስፋፊያ፣የጤናና የትምህርት ብድሮችን ሰጥተናል ብለዋል፡፡


4500 አባላት እንዳሉት የሚናገረው ተቋሙ አባል በመሆንና በየወሩ ከ500 ብር ጀምሮ በመቆጠብ የእነዚህ ብድሮች ተጠቃሚ መሆን ጠቅሷል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….




ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page