top of page

በኢትዮጵያ የባህል፣ የኪነ - ጥበብ እና የስፖርት ዘርፍ የአስተዳደር መዋቅር ወጥነት አለመኖር ፣ የመረጃ አያያዝ ችግር እና የሃብት ብክነት ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደጎዳው ጥናት አሳየ።

  • 47 minutes ago
  • 1 min read

ነሐሴ 5 2018


በኢትዮጵያ የባህል፣ የኪነ - ጥበብ እና የስፖርት ዘርፍ የአስተዳደር መዋቅር ወጥነት አለመኖር ፣ የመረጃ አያያዝ ችግር እና የሃብት ብክነት ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደጎዳው ጥናት አሳየ።


ባህል እና ስፖርት በፌዴራል እና በክልል ደረጃ እንኳን ወጥ የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር እንደሌለው ጥናቱ አሳይቷል።

ጥናቱ በጅማ ዩንቨርስቲ አስተባባሪነት የተሰራ ሲሆን የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ደጀኔ ገመቹ ባህል ፣ ኪነ-ጥበብ እና ስፖርት ለሀገር የጂ.ዲ.ፒውን (GDP) 4 ነጥብ 7 የኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ቢያበረክቱም ትኩረት አልተሰጠውም ብለዋል።


ጥበብ እና ባህልን ለይቶ በሳይንሳዊ መንገድ መመደብ በኢትዮጵያ እስካሁን ያልተሰራ ሥራ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ደጀኔ ገመቹ ነግረውናል ።


ይህም በዘርፉ ጥናትና ምርምር ላይ እስከዛሬም ፈተና ሆኖ የቆየ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።


ፕሮፌሰር ደጀኔ በሀገር ደረጃ የትኛው ዘርፍ ምን ዓይነት አስተዋፅኦ ያበረክታል የሚለውን የሚያስረዳ የተደራጀ የመረጃ ቋት የለንም ብለዋል።


ይህም ለባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ስፖርት ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ የምንሰጠው ቦታ ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ይላሉ።


ይህ ጥናት ሁሉንም የኢትዮጵያ ክልሎች ያካተተ ሲሆን 90 በመቶ ከሚሆኑ ዞኖች መረጃ መሰብሰቡን ባለሙያው ነግረውናል።


ከእነዚህም ቦታዎች ለጥናቱ ግብአት ከ4 ሺህ በላይ ናሙናዎች ተሰብስበዋል ተብሏል።


ለባህል ፣ ጥበብና ስፖርት ዘርፍ መዋቅራዊ ወጥነትን የሚያመጣ ፣ ያሉ ሀብቶችን በሙሉ አቅም ለመጠቀምና የመረጃ አያያዝን ለማዘመን የሚያግዝ ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ጥናቱ ጠቁሟል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....


ንጋት መኮንን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page