አማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ80000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ከ14000 በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን የወረዳው ግብርና ቢሮ ተናገረ፡፡
- 2 hours ago
- 1 min read
ነሐሴ 5 2018
አማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ80000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ከ14000 በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን የወረዳው ግብርና ቢሮ ተናገረ፡፡

ከሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ ባለመጣሉ በወረዳው የሚገኙ 10 ቀበሌዎች ለከፍተኛ ድርቅ መጋለጣቸውና በዚህም ምክንያት ከ14000 በላይ የቁም እንስሳት መሞቻቸውን ሰምተናል፡፡
ከ80000 በላይ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍል ጉዳት እንደደረሰባቸው በዚህም ድጋፍ እንደሚሹ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገዛአብ እያሱ ነግረውናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የጤና ችግሮች በቀበሌዎቹ እየታዩ እንደሆነም ሃላፊው ያስረዳሉ፡፡
ከጤናው ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች በመኖራቸው የተከሰተው በሽታ ምን ይሆን? የሚለውን ለመለየት ይህንን የሚከታተል ግብረ ሀይል መቋቋሙንና አዲስ ጥናት እየተደረገ እንደሆነም አቶ ገዛአብ ነግረውናል፡፡
በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ9000 በላይ ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ ሰብል መብቀል እንዳልቻለም ከሃላፊው ሰምተናል፡፡
አስቸኳይ የምግብ እና የውሃ እንዲሁም ለእንስሳት መኖ ለማቅረብ ያለው ሁኔታው ከወረዳው አቅም በላይ በመሆኑ የሌሎችም ድጋፍ እንሻለን፡፡
በዚህም መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲያግዙት ወረዳው ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
ማርታ በቀለ
_edited.jpg)



Comments