top of page

ነገ አርብ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች፣

  • sheger1021fm
  • Sep 25
  • 1 min read
ree

የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እወቋቸው ብሏል፡፡


በዚህም መሠረት፦


• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣

• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣

• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣

• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣

• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣

• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣

• ከሐራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት፣

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣

• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ፣ እንዲሁም

• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከነገ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ ይዘጋል፡፡


በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ በመሆኑን አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አቅርቧል።


አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና ትብብር አድርጉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡


ትኩስ ወሬዎችን ፣ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ሙሉ የሸገር ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለማግኘት የሶሻል ሚዲያ ፔጃችንን አሁን ይቀላቀሉ።


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page