top of page

ነሐሴ 17፣2016 - በኮንሶ ዞን የሠገን ዙሪያ ወረዳ የታጠቁ ሀይሎች ሰሞኑን ባደረሱት ጥቃት 13 ሰዎች ገድለው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደማቸው ተሰማ፡፡

  • sheger1021fm
  • Aug 23, 2024
  • 1 min read

በኮንሶ ዞን የሠገን ዙሪያ ወረዳ የታጠቁ ሀይሎች ሰሞኑን ባደረሱት ጥቃት 13 ሰዎች ገድለው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደማቸው ተሰማ፡፡


በታጣቂዎቹ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡት 8ቱ የፖሊስ አባላት ሲሆኑ 5 ንፁሃንን ሰዎች እንደሆኑ ዞኑ ለሸገር ተናግሯል፡፡


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በኮንሶ ዞን የሠገን ዙሪያ ወረዳ የታጠቁ ሀይሎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ድንገት ጥቃት በመፈፀም የሰገን ከተማን ተቆጣጥረው ለ 5 ቀናት እንደቆዩ የኮንሶ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ ሀላፊ ሰራዊት ዲባባ ነግረውናል፡፡



ሀላፊው ‘’ፀረ ሠላም ሀይሎች’’ ሲሉ የጠሯቸው እና ማንነታቸው በግልፅ አልታወቁም ያሏቸው እነዚህ አካላት የሰገን ከተማውን ተቆጣጥረው በቆዩበት ወቅት በሰዎች ላዜ ካደረሱት ጥቃት በተጨማሪ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድመዋል ብለውናል፡፡


23 የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤት ቁሳቁሶች ዝርፊያ እና ውድመት እንደደረሰባቸውም ከሀላፊው ሰምተናል፡፡

የወረዳ አስተዳደር ህንፃ፣ ግብርና ጽ/ቤት፣ ፖሊስ ፅ/ቤት፣ የወረዳው ምክር ቤት አዳራሽ፣ ማዘጋጃ ህንፃና ትላልቅ ጄኔሬተሮች፣ የሆስፒታል ዲጂታል የህክምና ቁሳቁስ፣ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ውድመት ከደረሰባቸው መካከል ናቸው ተብሏል፡፡

ታጣቂዎቹ የዘረፏቸውን ንብረቶችን ወደ አጎራባች መዋቅሮችና ሀይበና ቀበሌ አሽሽተዋል ብለውናል፡፡


የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ሀላፊ ሰራዊት ዲባባ እንዳሉት ከሆነ መሰል ጥቃቶች በአካባቢው የሚደጋገም ነው፡፡


ለመሆኑ ጥቃት አድራሾቹ እነማን ናቸው፤ ዓላማቸውስ ምንድነው ያልናቸው ሀላፊው ‘’ዓላማቸው በግልፅ ይህ ነው ሊባል ባይቻልም፤ ነገር ግን ከዚህ በፊት ኢፍትሀዊ በሆነ መንገድ የልዩ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ የሚያነሱ አካላት እንደነበሩ እናስታውሳለን’’ ብለዋል፡፡


የከተማው ህዝብ በተፈጠረው ጥቃት ተደናግጦ ከከተማው ሸሽቶ እንደወጣም አቶ ሰራዊት ነግረውናል፡፡


በአሁን ሰዓት በከተማው የመከላከያ ሰራዊት እንደተቆጣጠረውም ተነግሯል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/5n8mfwyu


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page