top of page

ነሀሴ 11 2017 - ደራሲ፣ ተርጓሚ፣ ተዋናይ፣ ከያኒ፣ አርቲስት ደበበ እሸቱ  ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

  • sheger1021fm
  • Aug 18
  • 1 min read

አንጋፉው ከያኒ ዛሬ ነሐሴ 11/ 2017ዓ.ም በ83 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተናግሯል።


ደበበ እሸቱ በደራሲነት፣ በተዋናይነት፣ በአዘጋጅነት፣ በቴአትር አስተዳደር እና የማኅበር መሪነት በሀገር ውስጥ፣ በአፍሪካ እና በአለም መድረክ ኢትዮጵያን ያገለገሉ ቀዳሚ ከያኒ መሆናቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ree

አበርክቶ ካደረጉባቸው ሥራዎች መካከል ያላቻ ጋብቻ፣ ሮሚዎና ዡልየት፣ ጠልፎ በኪሴ፣ ዳንዴው ጨቡዴ፣ አዳ ኦክ ኦራክል፣ የበጋ ሌሊት ራዕይ፣እናት ዓለም ጠኑ፣ ኪንግ ሊር፣ የአዘውንቶች ክበብ፣ የቬኒሱ ነጋዴ፣ ናትናኤል ጠቢቡ ድብልቅልቅ፣ ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር፣ ሻፍት ኢን አፍሪካ፣ ጉማ፣ የደም እምባ፣ የእምነቴ ፈተና ይጠቀሳሉ ሲል ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።


በታንዛኒያ፤ ኡጋንዳ፤ ኬንያ፤ ማላዊ፤ ኮንጎ ብራዛቪል፤ አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤ አይርላንድ፤ ብራዚል፤ ሰሜን አሜሪካ፤ እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ ካናዳ በመዘዋወር ለሞያቸው እና ለሀገራቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ መድረጋቸውም ተጠቅሷል።


ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፣ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም የአርቲስቱ አድናቂዎች፣ወዳጆች ሀዘናቸውን በማህበራዊ ሚዲያ እየገለፁ ነው።


ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በአንጋፋው ከያኒ ደበበ እሸቱ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰባቸው እንዲሁም ለአድናቂዎቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

2 Comments


Brian Dotts
Brian Dotts
Oct 08

I feel more confident in my trading since I started using https://cryptorobotics.ai/ — the automation removes a lot of the guesswork.

Like

Jiya Saxena
Jiya Saxena
Aug 18

For moments when you seek more than just a fleeting presence, our exquisite Call Girl in Delhi offer true companionship. They are sophisticated, charming, and dedicated to providing an unforgettable experience. Discover discretion and genuine connection, transforming your ordinary night into something truly special.


Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page