በኢትዮጵያ በፋይናንስ ተቋሞች የተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ከ176 ሚሊየን በላይ ደርሷል።
- 2 hours ago
- 1 min read
ሚያዝያ 20/2018
በኢትዮጵያ በፋይናንስ ተቋሞች የተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ከ176 ሚሊየን በላይ ደርሷል።
ከዚህ የባንክ ሂሳብ 97 በመቶው ግን ከ100 ሺህ ብር በታች ገንዘብ የተቀመጠበት መሆኑ ተነግሯል።
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋሞች በኪሳራ ምክንያት ቢዘጉ ገንዘቡን የቆጠበው ሰው ያስቀመጠውን እንዳያጣ ለመካስ በሚል የተቋቋመው የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ስራ ከጀመረ ሶስት ዓመት ሆኖታል።
ፈንዱ በዚህ ጊዜ ከባንኮችና ሌሎች የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የሰበሰበው የአረቦን ገንዘብ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተነግሯል።
ከጠቅላላ አረቦኑ አብዛኛው ወይም 10.41 ቢሊዮን ብሩ ከግል ባንኮች የተሰበሰበ እንደሆነ ፈንዱ ከላከልን መረጃ ላይ ተመልክተናል።
9.96 ቢሊዮን ብሩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ቀሪው 0.24 ቢሊየን ብር ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት የተሰበሰበ ነው ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ 31 የንግድ ባንኮችና 64 የማይክሮ ፋይናንስ ተቋሞች ከአማካይ ቁጠባቸው 0.3 በመቶውን በአረቦን መልክ ለፈንዱ ይከፍላሉ።
ፈንዱም ባንኮች እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኪሳራ ቢዘጉ የቆጣቢውን እስከ 100 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ይመልሳል።
ግን ከፈንዱ ለቆጣቢዎች የሚመለሰው የገንዘብ ጣራ ለምን 100ሺህ ብር ብቻ ሆነ የሚል ጥያቄ ሲነሳ ይሰማል።
ይህንን እና ሌሎች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለተቋሙ የስራ ሀላፊ አንስተናል።
ቴዎድሮስ ወርቁ





Comments