ሰኔ 5 2017 - ዛሬ በምክር ቤት ሹመታቸው የፀደቀላቸው የምርጫ ቦርድ የስራ ሀላፊዎች ቀጣዩን ምርጫ ፍትሃዊ ና ታዓማኒ ለማድረግ እንዲሰሩ ተጠየቁ
- sheger1021fm
- 1 day ago
- 1 min read

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ በካሄደው መደበኛ ጉባኤው ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው ሲገለግሉ የቆዩትን አቶ ተስፋዬ ንዋይን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሆኑ የቀረበለትን ውሳኔ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ስበሰባው በትግራይ ክልል በተለያዩ ሃላፊነት ላይ የሰሩትን፤ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው ሲገለግሉ የቆዩትን አቶ ተክሊት ይመስል እና በሃረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ዳኛ ሆነው ሲገለግሉ የቆዩትን ወ/ሮ ነሲም አሊ የቦርድ አባል እንዲሆኑ የቀረበለትን ውሳኔ አጽድቋል፡፡
ሹመታቸውን በተመለከተ ሃሳባቸውን የሰጡት የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር አበባው ደስአለው ነፃ እና ገለልተኛ ምርጫ ማካሄድ የምርጫ ቦርድ ዋነኛ ስራው ቢሆንም እስካሁን ባለው ሁኔታ ነፃ እና ገለልተኛ ምርጫ አለመካሄዱን የተለያዩ አካላት በቅሬታ እንደሚቀርቡ ተናግረው ተሿሚዎቹ ተቀጣዩን ምርጫ ነፃ እና ተአማኒ ለማድረግ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ሌላው የምክር ቤት አባል አቶ ኢሳ ቦሩ በበኩላቸው አዲስ ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅትም ሆነ በስራ ልምድ ብቁ መሆናቸውን ተናግረው ቀጣዩን ምርጫ ግልጽ እና ፍትአዊ የማድረግ አቅም እንዳላቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ቤልጅጌ ተሿሚዎችን በተመለከተ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት መካሄዱን ተናግረው በህገ-መንግስቱ እና በምርጫ ህጉ መሰረት አዲሶቹ ሃላፊዎች የሚካሄዱ ምርጫዎችን እና ህዝብ ውሳኔዎችን ገለልተኛ ሆኖ ለማካሄድ ይሰራሉ ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments