top of page

ሰኔ 5 2017 - ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነና ለበርካታ ህፃናት የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል የተባለ የልብ ህክምና መሳሪያ ተበረከተ

  • sheger1021fm
  • Jun 12
  • 1 min read
ree

የልብ ቀዶ ህክምናን ጨምሮ ሁሉንም የልብ ህክምናዎች በነፃ የሚሰጠው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል አገልግሎቶችን የሚሰጠው ከሚሰበስበው እርዳታ ከሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚደረግለት ድጋፍ መሆኑን ተናግሯል፡፡


ማዕከሉ የህክምና መሣሪያ ድጋፉን ያገኘው ላይፍ ፎር አፍሪካ ከተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የልብ ህክምና መሳሪያው ለማዕከሉ የመጀመሪያ የሆነና ለበርካታ ህፃናትን በቀዶ ህክምና ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነ የነገሩን የማዕከሉ የህዝብ ግንኙነት ዶክተር ዳዊት እሸቱ ናቸው፡፡


የተደረገው የክምና መሳሪያ ድጋፍ የልብ ቀዶ ህክምናው ከተከወነ በኋላ ልብ ሳይዘጋ ምን ያህል ለውጥ መጥቷል የሚለውን ለማየት የሚያግዝና ቀዶ ህክምናው ሳይጠናቀቅ ችግር ካለ ለመለየት የሚረዳ በመሆኑ ተደጋጋሚ ቀዶ ህክምና እንዳይደረግና ስራውንም የሚጠይቀውንም ወጪንም የሚቆጥብ ነው ተብሏል፡፡

ላለፉት 7 ዓመታት ማህበራዊ ሚዲያ ለሰብዓዊነት በመጠቀም ማዕከሉን ስትረዳ በቆየችው በጎ አድራጊ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ በተመሠረተው ላይፍ ፎር አፍሪካ ተቋም የህክምና መሳሪያው መለገሱ ተነግሯል፡፡


የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነና የነጻ የልብ ህክምና የሚሰጥ ማዕከል ሲሆን ማእከሉ ከመንግስት ምንም አይነት በጀት የማይመደበለትና ከተለያዩ ተቋማትና በጎ ፈቃደኞች በሚያገኘው ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ነው ተብሏል፡፡

በተለይም ስራውን ለማስፋፋት በቂ የልብ ቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ቢኖሩትም የግብዓት እጥረት ግን ትልቅ ፈተና እንደሆነበት ተነግሯ፡፡


በአሁኑ ሰአትም በማዕከሉ ከሰባት ሺ በላይ ሰዎች የልብ ህክምና ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡


ምህረት ስዩም

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page