top of page

ሰኔ 30 2017 - በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን ለመቆጣጠር በወጣው  አዋጅ ላይ ''መርማሪው ከግድያ ውጭ የትኛውንም ድርጊት ቢፈጽም ተጠያቂ አይሆንም'' የሚለው ድንጋጌ  እንዲወጣ ተደረገ

  • sheger1021fm
  • Jul 7
  • 1 min read

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው  አዋጅ ላይ መርማሪው ከግድያ ውጭ የትኛውንም ድርጊት ቢፈጽም ተጠያቂ አይሆንም የሚለው ድንጋጌ  እንዲወጣ ተደረገ፡፡


ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ በልዩ ስብሰባው፤ ከአሁን በፊት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አርሞ አፅድቋል፡፡


የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 37ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፤ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1387/2017 አድርጎ ማፅደቁን አስታውሰዋል፡፡

ree

ከአሁን በፊት የነበረው የረቂቅ አዋጅ ድንጋጌ እንዲታረም መደረጉ አተገባበሩ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያስከትል ስለሚችል ረቂቅ አዋጁን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ሩ አቶ ኢሳ ቦሩ አስረድተዋል፡፡


የምክር ቤት አባላት አዋጁ ለሰብአዊ መብት ጥሰት በር የሚከፍት በመሆኑ ድንጋጌውን መሻሻሉ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ሰኔ 10/2017 ዓ.ም የጸደቀው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ ነበር፡፡


አዋጁ በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ (Under cover investigation) እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያትና ከፈቃዱ ውጪ በሆኖ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም ማለቱ ከፍተኛ ትችትና ተቃውሞ ቀርቦበት ነበር።


አሁን ይህ ከግድያ ወንጀል በስተቀር መርማሪው ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም የሚለው አንዲወጣ ተደርጎ አዋጁ ተሻሽሎ ጸድቋል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page