ሰኔ 26 2017 - የሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና ባለድርሻ አካላት ዳግም በትግራይ ጦርነት እንዳይነሳ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠ/ሚኒስትሩ አሳሰቡ
- sheger1021fm
- Jul 3
- 1 min read
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ማሳሰብያ የሰጡት ዛሬ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡
አቶ ሳዲቅ አደም የተባሉ የምክር ቤት አባል በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት መኖሩን ተናግረው፤ በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራርያ እና ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡
ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው በማለት የተናገሩት የምክር ቤት አባሉ ከሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ ምሁራን እና ወጣቶች ምን ይጠበቃል? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሰጡት ምላሽ የሁሉም እምነት አባቶች እዚህ ተወካይዎች አላችሁ፣ ሌላ ምንም ስራ የላችሁም በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት፣ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፣ ከተጀመረ ወዲያ ብትናገሩ ዋጋ የለውም ብለዋል፡፡
ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ ኤምባሲዎች ውጊያ እንዳይጀመር አሁን ሚናቸውን ተወጡ ያሉት ዐቢይ አህመድ ምክንያቱም ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደነበረው አይደለም ነገር ይበላሻል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በእኛ በኩል በትግራይ ምድር እንድ ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የለንም፣ ከቻልን ማልማት ነው የምንፈልገው ብለዋል፡፡
ትግራይ ላሉ ሃይሎችም ለትግራይ ህዝብም፣ ለኢትዮጵያ ህዝብም መታወቅ ያለበት ጦርነት አያስፈልገንም በሰለም እና በውይይት ችግሮችን መፍታት ይቻላል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6








