top of page

ሰኔ 26 2017 - ''ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት ጋዝ አምርታ ለአለም ገበያ እንደምታቀርብ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ

  • Jul 3, 2025
  • 1 min read

ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት ጋዝ አምርታ ለአለም ገበያ እንደምታቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡


የጋዝ ማስተላለፊያ መሰረተ ልማቱም በሶማሌ ክልል ተገንብቶ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው ተናግረዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመጪው ዓመት መጀመሪያም ለገበያ ይቀርባል ሲሉ የተናገሩት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ከእንደራሴዎቹ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡ ጊዜ ነው፡፡


በተጨማሪም ከናይጀርያው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር በተደረገ ስምምነት በጥቂት ወራት ውስጥ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት ትጀምራለችም ብለዋል፡፡


ፋብሪካው በሶስት ዓመት ከመንፈቅ ተጠናቅቆ ይመረቃል ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል የወርቅ ምርት ከአምናው በብዙ እጥፍ አድርጎ ዘንድሮ 3.5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቶበታል ብለዋል፡፡


አምና የተመረተው እና ለአለም ገበያ የተላከው ወርቅ 4 ቶን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድሮ 37 ቶን በመላክ ነው ከፍተኛ የተባለ የውጪ ምንዛሪ የተገኘው ብለዋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Recent Posts

See All
የሐምሌ 18 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ስፔን በስፔኗ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ አቅረቢያ ነዋሪዎች በመዛመት ላይ በሚገኘው ከባድ የሰደድ እሳት ምክንያት ለቅቀው እንደወጡ ታዘዙ፡፡ የማድሪድ ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ የሰደድ እሳቱ በጣሙን ያየለበት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እስከ ትናንት ምሽትም ከ19 ሺህ በላይ ሰዎች ለቀው መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡ በስፔን ወቅታ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page