ሰኔ 24 2017 - ኢትዮጵያ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት(AI)
- sheger1021fm
- Jul 1
- 1 min read
ከሰሞኑ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ( #Artificial_Intelligence ) የተሰሩ አጫጭር ተንቀሳቃሽ ምስሎች ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቆታል፡፡
ጥናታዊ ፅሁፍ፣ የማስታወቂያ ስራው ሌላ ሌላውም ‘’አርተፊሻል ኢንተለጀስ’’ን የማይሰራው የለም በሚባል ደረጃ ይነገርለታል፡፡
ይህም ‘’የሰው ልጅ ስራ በመንጠቅ አደጋ ደቅኗል’’ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ‘’አይ ጥሩ እገዛ እያደረገ ነው’’ በሚልም ይሞካሻል፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ለዚህ ዘመን አመጣሽ ፈጠራ ምን ያህል ተዘጋጅታለች?

የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ቴክኖሎጂው ያመጣውን ችግር በራሱ በቴክኖሎጂው መፍታት እንችላለን ይላሉ፡፡
የፊልም ባለሞያ እና መምህሩ እንዳለ ደምሰው ደግሞ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ እነ ሆሊዎድን ሳይቀር የዓለማችንን ታላላቅ የፊልም ኢንዱስትሪ ስጋት ውስጥ የከተተ በመሆኑ ወትሮም በብዙ ችግር ውስጥ ያለው የሃገራችን ሲኒማ የወደፊት ዕጣ ፈንታም ጥያቄ ውስጥ ነው ይላሉ፡፡
በአካል ግዛቸው(ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ክፍል ኃላፊ ናቸው፡፡ እርሳቸው ኢትዮጵያ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ወደኋላ እንዳትቀር አሁን ከዓለም እኩል መራመድ አላባት የሚል ሃሳብ አላቸው፡፡
ባለሞያው ቴክኖሎጂው በሃገር ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ለመቀነስ ለሰዎች ግንዛቤ መስጠት ትልቁ መፍትሔ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX












Comments