ሰኔ 18 2017 - በምርት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት አንድ እንቁላል እስከ 25 ብር እንዲሸጥ እድል ፈጥሯል ተብሏል
- sheger1021fm
- Jun 25
- 1 min read
በዶሮ እርባታ ላይ የተሰማሩ ትናንሽ አርቢሮች ከዘርፉ መውጣታቸው ለእንቁላል መወደድ ምክንያት ሆኗል ተባለ።
አርቢዎቹ ከዘርፉ እንዲወጡ ያስገደዳቸውም የመኖ ዋጋ ውድነት እንደሆነ ሰምተናል።
መኖ አቅራቢ ፋብሪካዎችም ቢሆኑ በጥሬ እቃ እጥረት እና መወደድ ምክንያት እየተቸገሩ መሆኑን ሰምተናል።
በዚህ እና በሌሎች ተደራራቢ ምክንያቶች የእንቁላል መኖ ዋጋ ከፍ ማለቱን ተነግሯል።
አንድ ኩንታል የእንቁላል ጣይ የዶሮ መኖ ከሁለት ወር በፊት ሲሸጥ ከነበረው 4,800 ብር አሁን 5,800 ብር እየተሸጠ መሆኑን ሰምተናል፡፡
በተለይ አቅም የሌላቸው ትናንሽ አርቢዎች እየተቸገሩ በመምጣታቸው ከገበያው ለመውጣት ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን በምርት እና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት አንድ እንቁላል እስከ 25 ብር እንዲሸጥ እድል ፈጥሯል ተብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ መኖ አቅራቢ ፋብሪካዎችም በብዙ ይፈተናሉ የተባለ ሲሆን ለመኖ ማቀነባበሪያ የሚውሉ ግብዓቶችን አለማግኘት ዋነኛ ችግራቸው እንደሆነ ተነግሯል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il












Comments