top of page

ሰኔ 17 2017 - የኢንጂነር አልቤርቶ ቫርኔሮ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በጣሊያን ሀገር ተፈፀመ

  • Jun 24, 2025
  • 1 min read

ለአዲስ አበባ ምልክት የሆኑ ህንፃዎችን በማነፅ የሚታወቁት ኢንጂነር አልቤርቶ ቫርኔሮ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በጣሊያን ሀገር ተፈፀመ።


ለኢንጂነር  ቫርኔሮ ዛሬ በአዲስ አበባ ለገሃር አካበቢ በሚገኘው መድሃኒአለም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የስንብት ፕሮግራም በቫርኔሮ ኮንስትራክሽን ሰራተኞች ተደርጎላቸዋል።


ኢንጂነር ቫርኔሮ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ነበሩ።


የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል ካነጿቸው  መካከል ይጉኙበታል።


በቅርቡም የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሰርተዋል።


ባለፈው ሳምንት አርብ የህልፈታቸው ወሬ የተሰማው ኢንጂነር ቫርኔሮ በዛሬው እለት ቀብራቸው መፈፀሙን ሰምተናል።

Recent Posts

See All
የሐምሌ 18 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ስፔን በስፔኗ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ አቅረቢያ ነዋሪዎች በመዛመት ላይ በሚገኘው ከባድ የሰደድ እሳት ምክንያት ለቅቀው እንደወጡ ታዘዙ፡፡ የማድሪድ ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ የሰደድ እሳቱ በጣሙን ያየለበት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እስከ ትናንት ምሽትም ከ19 ሺህ በላይ ሰዎች ለቀው መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡ በስፔን ወቅታ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page