top of page

ሰኔ 14፣ 2016 - ምቹ የስራ ከባቢን መፈጠር ጥቅሙ ለሰራተኛዉ ብቻ ሳይሆን አሰሪዉ እና መንግስት ከግባቸዉ እንዲደርሱ ድርሻው ከፍተኛ ነዉ ተባለ

  • Jun 21, 2024
  • 1 min read

ምቹ የስራ ከባቢን መፈጠር ጥቅሙ ለሰራተኛዉ ብቻ ሳይሆን አሰሪዉ እና መንግስት ከግባቸዉ እንዲደርሱ ድርሻው ከፍተኛ ነዉ ተባለ፡፡


ሰራተኛዉ ተረጋገቶ እንዲሰራ፣ አሰሪዉም ከሰራተኛዉ የሚፈልገዉን ለማግኘት፣ መንግስትም ሀገሪቱ ወደ መካካለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ የወጠነዉ ግብ እንዲሳካ ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያነጋገርናቸዉ ተመራማሪዎች ነግረዉናል፡፡


የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ እና መምህር ኢዛና አምደወርቅ(ዶ/ር) ምቹ የስራ ከባቢ ከሌላቸዉ የስራ መስኮች ዉስጥ አንዱ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት አምራች ኢንዱስትሪ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡


ተመራማሪዉ በመስኩ ላይ በተሰራ ጥናት ከፍተኛ የሰራተኛ ስራ መልቀቅ እንደ ሚታይ እና አዲስ ሰራተኛ የሚቀጠርበትም ነዉ ይላሉ፡፡


የፋብሪካ የስራ ሃላፊዎችን አነጋግረን በሰራነዉ ጥናት በሳምንት ዉስጥ ቀላል የሚባልዉን ጊዜቸዉን የሚሰለፉት በአዲስ ሰራተኛ ምልመላ መሆኑን ነግረዉናል ብለዋል፡፡


ይህም አንድ ሰራተኛ ተረጋግቶ እንዳሰራ ከማድረጉም በላይ አሰሪዉ ከሰራተኛዉ የሚፈገን እንዳያገኝ እንደሚደርገዉ ተናግረዋል።



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page