ሰኔ 13 2017 - ዳሸን ባንክ የከበሩ ንብረቶችን የማስቀመጥ አገልግሎት መጀመሩን ተናገረ።
- sheger1021fm
- 4 hours ago
- 1 min read
ዳሸን ባንክ የከበሩ ንብረቶችን የማስቀመጥ አገልግሎት መጀመሩን ተናገረ።
እንደ ዋስትና ሠነድ፣ ዕንቁ፣ የከበሩ ድንጋዮችን ጨምሮ ሌሎች ውድ ዋጋ ያላቸውን የከበሩ ንብረቶችን የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ አስረድቷል፡፡
የዳሸን ባንክ የውድ ንብረቶች ማስቀመጥ አገልግሎት ዘመኑ ባፈራቸው የደህንነት መሳሪያዎች የተደራጀ መሆኑን የባንኩ
ትሬዠሪ ማኔጅመንት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አንዱዓለም አስረድተዋል።

ባንኩ አገልግሎቱን እንዲጀምር በተለያየ ጊዜ ከደንበኞች ጥያቄ ሲቀርብለት እንደነበርም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
በተለይም የማዕድን ዘርፉ ላይ ለተሰማሩ የባንኩ ደንበኞች ታቅዶ የቀረበው ይህ አገልግሎት ደንበኞች እንደፍላጎታቸው ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ሳጥን ወይም ካዝናዎችን ከባንኩ በመከራየት እንደ ወርቅ፣ የከበሩ ማዕድናት፣ ፓስፖርት፣ የጋብቻ ሰርተፊኬቶች ሌሎች ውድ የሆኑ ንብረቶችን የሚያስቀምጡበት እንደሆነ አቶ አንዱዓለም ተናግረዋል፡፡
የግለሰብ ደንበኞችም ሆኑ ተቋማት በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች ቀርበው አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ሲጨርሱ ወደ ዋና መሥሪያ ቤት ቀርበው አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
የዚህ አገልግሎት ደንበኞች ለዚሁ የሚሆን ልዩ መታወቂያ ይዘጋጅላቸዋል መባሉንም ሰምተናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários