top of page

ማስረጃ ሳይቀርብ፣ እንዲሁም መከፈል ካለበት በብልጫና ድጋሚ በተፈፀመ ክፍያ የተለያዩ መ/ቤቶች በቢሊዮን የሚቆጠብ ብር ያላግባብ ወጪ ማድረጋቸው ተረጋገጠ፡፡

  • 5 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 11/2018


የሒሳብ አያያዝ መመሪያዎችን በመጣስ ማስረጃ ሳይቀርብ፣ እንዲሁም መከፈል ካለበት በብልጫና ድጋሚ በተፈፀመ ክፍያ የተለያዩ መ/ቤቶች በቢሊዮን የሚቆጠብ ብር ያላግባብ ወጪ ማድረጋቸው ተረጋገጠ፡፡


የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2017 የሒሳብ ምርመራ ሪፖርት እንደሚያሳየው የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጭ ተመዝግቦ የተገኘ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ፣ ማስረጃ ሳይቀርብ ወጪ የተደረገ 35.8 ሚሊዮን ፣ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ወጭ ደግሞ 57.8 ሚሊዮን ብር እና በብጫና ድጋሚ ያላግባብ በተፈፀመ ክፍያ 280.6 ሚሊዮን ብር ያለአግባብ ከመስሪያ ቤቶች ወጪ ተደርጎ መገኘቱን ጠቅሷል፡፡

መመሪያ ተጥሶ መከፈል ካለበት በብልጫና ድጋሚ ያላግባብ ክፍያ ፈፅመዋል ከተባሉት መካከል፡-


ጤና ሚኒስቴር 231.1 ሚሊዮን ብር፣


የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 23 ሚሊዮን ብር፣


የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ፣


የቃሊቲ ጉምሩክ ቅፅ/ቤት 2.4 ሚሊዮን ብር፣ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲ 2.1 ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረጉ መሆኑ በሒሳብ ምርመራው ተረጋግጧል ተብሏል፡፡


እንዲሁም የተሟላ የወጭ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጭ ተመዝግቦ ከተገኘው 1.1 ቢሊዮን ብር በላይ መካከል፡-


የሞያሌ ጉምሩክ 25.4 ሚሊዮን ብር፣


የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት 23.4 ሚሊዮን ፣


የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት 7.5 ሚሊዮን ፣


የማዕድን ልማት ኢንስቲትዩት 6.6 ሚሊዮን፣


የማዕድን ሚኒስቴር ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ እና


የባህር ዳር የጉምሩክ 4.7 ሚሊዮን ከፍተኛውን ድርሻ የያዙ ናቸው ተብሏል፡፡


ያለበቂ ማስረጃ ክፍያ መፈፀምን ጨምሮ ደንብና መመሪያ ተጥሶ የሚፈፀሙ ክፍያዎች ተጠያቂነትን ያስከትላሉ ያለው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ገንዘቡ ተመላሽ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Recent Posts

See All
አሐዱ ባንክ “አሐዱ ለኩሉ'' እና ''ማኅደር" የተባሉ ሁለት መተግበሪያዎችን በይፋ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ።

ሰኔ 11/2018 አሐዱ ባንክ “አሐዱ ለኩሉ'' እና ''ማኅደር" የተባሉ ሁለት መተግበሪያዎችን በይፋ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ። ሁለቱ የሞባይል መተግበሪያዎች የባንኩን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ጉዞን ይበልጥ እንደያጠናክሩለት እንደሆኑ ተነግሯል። "አሐዱ ለከሉ "የተባለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ደንበኞች ሞባ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page