አሐዱ ባንክ “አሐዱ ለኩሉ'' እና ''ማኅደር" የተባሉ ሁለት መተግበሪያዎችን በይፋ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ።
- 2 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 11/2018
አሐዱ ባንክ “አሐዱ ለኩሉ'' እና ''ማኅደር" የተባሉ ሁለት መተግበሪያዎችን በይፋ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ።
ሁለቱ የሞባይል መተግበሪያዎች የባንኩን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ጉዞን ይበልጥ እንደያጠናክሩለት እንደሆኑ ተነግሯል።
"አሐዱ ለከሉ "የተባለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ደንበኞች ሞባይል ስልካቸውን በመጠቀም የሒሳብ መረጃቸውን እንዲያዩ፣ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ፣ እንዲያስተዳድሩ፣ የገንዘብ ፍሰታቸውን እንዲከታተሉ እና የተለያዩ የክፍያ አገልግሎቶችን ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲያከናውኑ የሚያስችል መሆኑን በባንኩ መግለጫ ተጠቅሷል።
የደንበኞችን የአጠቃቀም ሒደቶች በመተንተን በብዛት የሚጠቀሙባቸውን አገልግሎቶች በቅድሚያ እንዲያዩ የሚያስችል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ሥርዓትን በውስጡ ያካተተ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ፤ ደንበኞች ሳምንታዊ የወጪ ሪፖርታቸውን/ መግለጫዎችን በማየት የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እንዲገመግሙ እና የተሻለ የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዲወስኑም ያግዛቸዋል ተብሏል።
“አሐዱ ለኩሉ" በዓለም አቀፍ የደኅንነት መሥፈርቶች መሠረት የተገነባ ሲሆን፤ ማጭበርበርን እና የሳይበር ስጋቶችን ለመከላከል የተለያዩ የደኅንነት ሥርዓቶችን ያካተተ መተግበሪያ ነው።
''አሐዱ ለኩሉ" በአሐዱ፡ባንክ የውስጥ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ እና በቀጣይም እየተሻሻለ የሚሔድ መተግበሪያ ሲሆን፤ ይህም ባንኩ ቴክኖሎጂን የመፍጠር አቅሙ በአያሌው እንዳሳደገ ያሳየ መተግበሪያ ነው፡፡
"ማኅደር” በሚል መጠሪያ በዛሬው እለት አሐዱ ባንክ በይፋ ያስጀመረው መተግሪያ ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት የንግድ ክዋኔዎችን የሚመዘግቡበት እና የሚተዳደሩበትን፣ ብድር የሚጠይቁበትን፤ የንግድ መድን ሽፋን የሚያገኙበትን አጠቃላይ ሥራዎች በአንድ ያቀፈ ነው ተብሏል።
“ማኅደር የንግድ ተቋማት ራሳቸውን በዲጂታል መንገድ እንዲመዘግቡ ፤ የሽያጭ፣ የወጪ እና ሌሎች ከንግድ ሥራቸው ጋር የተያያዙ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን የሚመዘግቡበት የዲጂታል የገንዘብ መመዝገቢያን (Cash Book) አብሮ ያካተተ መሆኑ ተጠቅሷል።
“ማኅደር" የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት የንግድ አቅማቸውንና የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን መሠረት በማድረግ ብቻ ካለምንም የብድር ማስያዣ እስከ 600,000 ብር ድረስ የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያችላል ተብሏል።
ንጋቱ ሙሉ





Comments