top of page

ሚያዝያ 30 2017 - የነዳጅ ክፍያን በኤም-ፔሳ ሳፋሪኮም መክፈል ተጀመረ።

  • May 8, 2025
  • 1 min read

የኤም ፔሳ ሳፋሪኮም ደንበኞች ለመኪናቸው ለሚገዙት ነዳጅ ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ትናንት በአዲስ አበባ ቦሌ ቶታል ኢነርጂስ ነዳጅ ማደያ አስጀምሯል።


አገልግሎቱ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ ክፍያ በፍጥነት እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ የሞባይል ስልኮቻቸውን ተጠቅመው እንዲፈፅሙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ የM-PESA ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤልሳ ሙዞሊኒ "ዛሬ በዲጂታል መፍትሄዎች ህይወትን ለማቃለል በምናደርገው ጉዞ ውስጥ ሌላ አስደሳች እርምጃ ተራምደናል ብለዋል።


በኤም ፔሳ ሳፋሪኮም የነዳጅ ክፍያ መፈፀሚያ መላ ለአጠቃቀም ምቹ ሆኖ የቀረበ መሆኑም ተነግሯል።


ይህንን የነዳጅ የክፍያ መላን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ በርኦ ሀሰን እና የኤም ፔሳ ሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤልሳ ሙዞሊኒ አስጀምረውታል።


ንጋቱ ሙሉ

Recent Posts

See All
የሐምሌ 18 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ስፔን በስፔኗ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ አቅረቢያ ነዋሪዎች በመዛመት ላይ በሚገኘው ከባድ የሰደድ እሳት ምክንያት ለቅቀው እንደወጡ ታዘዙ፡፡ የማድሪድ ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ የሰደድ እሳቱ በጣሙን ያየለበት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እስከ ትናንት ምሽትም ከ19 ሺህ በላይ ሰዎች ለቀው መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡ በስፔን ወቅታ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page