top of page

መጋቢት 11 2017 - የህዝብ እንደራሴዎች በ2017 ግማሽ የበጀት ዓመት ብቻ 28 አዋጆችን አፅድቀዋል፡፡

  • sheger1021fm
  • Mar 20
  • 2 min read

የህዝብ እንደራሴዎች በ2017 ግማሽ የበጀት ዓመት ብቻ 28 አዋጆችን አፅድቀዋል፡፡


ከእነዚህ ተከታትለው ከፀደቁ አዋጆች በተጨማሪ አሁንም በረቂቅነት ደረጃ የሚገኙም አሉ፡፡


በቅርቡ የተረቀቁ አዋጆች እንዲጸድቁ ለፓርላማው በቀረቡበት ወቅት ከ #ህገ_መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ አንቀፆች ይገኙባቸዋል በሚል በፓርላማ አባላት ትችትና ጥያቄ የተነሱባቸውም ነበሩ፡፡


ለአብነትም፤ በአዲሱ የሲቪል ሰርቪስ አዋጅ አንቀጽ 99 ንዑስ አንቀፅ 5 ላይ ስለይግባኝ የተደነገገው በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀፅ 6 ጋር ከተደነገገው እና በአዲሱ አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ አንቀፅ 28 ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ ስለ ቋንቋ የተቀመጠው በህገመንግስቱ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀፅ 2 ከተደነገገው ጋር አይጣረሱም ወይ የሚሉት ይገኙበታል፡፡


ለመሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተከታትለው እየወጡ ያሉ አዋጆች የየዘርፉ ባለሞያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻዎችን ሀሳብ እና ሞያዊ አስተያየት ያካተቱ ናቸው ወይ? ረቂቆቹ ምን ያህል ለባለሞያ ክፍት ናቸው?


ህዝቡስ እንዲያውቃቸው የተሰራ ስራ ይኖር ይሆን? በጉዳዩ ላይ የዘርፉ ባለሞያዎች እና የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎችን አነጋግረናል፡፡


ኤሌያስ ተስፋዬ በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ሲሆኑ፣ የህግ ባለሞያዎች እየወጡ ባሉ ህጎች ላይ ያላቸው ተሳታፊነት በቂ የሚባል እንዳልሆነ ያስረዳሉ፡፡ ረቂቅ አዋጆቹን በጊዜ አንብቦ አስተያየት ለመስጠትም ረቂቆቹን በጊዜ አለመገኘታቸው ሌላኛው ችግር እንደሆነ ያነሳሉ፡፡


በተለያዩ መንገዶች ያገኘናቸውን አዋጆችም ቢሆኑ አንዳቸውን ጊዜ ወስደን አንብበን ሳንጨርስ ሌላኛው ፀደቀ ሲባል እንሰማለን ብለውናል፡፡


ውስንነት ያለባቸው አዋጆች መሻሻልን የሚደገፉት ባለሞያው፤ አንድ #አዋጅ በቂ ውይይት ሳይደረግበት የሚወጣ ከሆነ ብዙ ሳይሰራበት እንደገኛ እንዲሻሻል መጠየቁ አይቀርም ያሉ ሲሆን በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታትም ይህ እንደታየ አስታውሰዋል፡፡


ይህ እንዳይገጥም ፓርላማውም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት አዋጆች ከመጽደቃቸው በፊት፤ እያንዳንዱ የተካተቱ ሀሳቦች ለህዝብ ምን ያህል ይጠቅማሉ የሚለው እንዲፈተሹ ማድረግ እንደሚገባቸውም መክረዋል፡፡


ree

የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት ያለው የሞያ ማህበር ነው፡፡ እየወጡ ያሉ አዋጆች ምን ያህል የህግ ባለሞያዎች ውይይት ያደርጉባቸዋ ስንል ማህበሩን ጠይቀናል፡፡


የማህበሩ ዋና ፀሀፊ ዘሪሁን ጴጥሮስ፣ በሚወጡ ረቂቅ አዋጆች ላይ የተለያዩ ባለሞያዎች የተካተቱበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ሞያዊ አስተያየታችን አናዋጣለን፤ ከፓርላማውም ጋር እንሰራለን ብለውናል፡፡


ይህ ማለት ግን በረቂቅ አዋጆቹ ላይ የምንሰጣቸው ሀሳቦች ሁሉም ተቀባይነት ይኖራቸዋል ማለት አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡


አንድ አዋጅ ከጸደቀ በኋላ ተፈጻሚ መሆን የሚጀምረው በፌደራል #ነጋሪት_ጋዜጣ ታትሞ ከመወጣት ቀን ጀምሮ ነው፡፡


በዚህ ዓመት የፀደቁ አዋጆች ግን እየታተሙ እንዳልሆነ ሰምተናል፡፡ በዚህም ባለሞያዎችም ሆኑ አዋጆቹን የሚፈልግ ሰው እያገኛቸው አይደለም ተብሏል፡፡


በሚወጡ አዳዲስም ሆነ ነባር ህጎች ሰዎች ግንዛቤ ኖሯቸው ለቅጣት እንዳይዳረጉ የግንዛቤ ስራ እንዲሰራ ሀላፊነት የተሰጠው ክፍል በፍትህ ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በሚወጡ ህጎች ላይ ምን ያህል ለህዝቡ የማሳወቅ ስራ እየሰራ እንደሆነ ጠይቀናል፡፡


በሚኒስቴሩ የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር እንዳልካቸው ወርቁ በተመረጡ የህግ ጉዳዮች ላይ ሰዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እየሰሩ እንደሆ ጠቅሰዋል፡፡


ነገር ግን በዚህም ዓመት በፀደቁ አዋጆች በአንዳቸውም ላይ ግንዛቤ የመስጠት ስራ አልሰራንም ብለውናል፡፡ ለዚህም ምክንያት ሲጠቅሱ አዋጆቹ ስለማይታተሙ እኛም እያገኘናቸው አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡



ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በውንድሙ ሀይሉ

Recent Posts

See All
ታህሳስ 3/2018 የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍጆታ ካለፈው ሃምሌ ወር ወዲህ እያደገ መጥቷል ተባለ።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች ከምታመርተው የኤሌክትሪክ ሃይል 90 በመቶው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል እንደሆነ ተጠቅሷል። በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ኢትዮጵያ ከውሃ እና ከነፋስ ከ15,300 ጊጋዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨቷ ተነግሯል። በየወሩ በአማካይ 3,800 ጊጋዋት ሰአት የኤ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page