top of page

መንግስት ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም በሚጀምረው በጀት ዓመት፤ ከታክስ ገቢ ወደ 1.5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ ታወቀ፡፡

  • Jun 11
  • 2 min read

ሰኔ 4/2018


መንግስት ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም በሚጀምረው በጀት ዓመት፤ ከታክስ ገቢ ወደ 1.5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ ታወቀ፡፡


በበጀት ዓመቱ መንግስት ለጠቅላላ ገቢ የውጪ ብድርን ጨምሮ ከ2 ትሪሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ዛሬ ወደ ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ የሚጠበቀው የፌደራል መንግስት የ2019 የገቢ በጀት ረቂቅ ሰነድ ያሳያል፡፡


በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ጠቅላላ ገቢ የውጪ ዕርዳታን ጨምሮ 1.8 ትሪሊዮን ብር እንደሚሆን ተገምቷል የሚለው ሰነዱ ይህም በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17.4 በመቶ እድገት ያለው እንደሆነ ዘርዝሯል፡፡


ከዚህ ውስጥ 1.5 ትሪሊዮን ብር ወይም 82 በመቶው ከታክስ ገቢ እንደሚሆን አስረድቷል፡፡


በዚህም መሰረት፡-

ጠቅላላ ገቢና ዕርዳታ 1,816,550,478,151 ብር፣


ከምንዳና ደመወዝ 97,346,528,758 ብር ፣


የአገር ውስጥ ቀጥታ ታክሶች 427,487,817,419 ብር፣


ከኪራይ ገቢ ግብር 2,589,596,337 ብር፣


ከኮርፖሬት ድርጅቶች የንግድ ሥራ ገቢ ግብር 263,009,567,243 ብር፣


ከገቢ ዕቃዎች የቅድሚያ ገቢ ግብር 26,627,285,968 ብር፣


ከአገር ውስጥ ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች 277,988,904,983 ብር፣


በአገር ውስጥ ከሚመረቱ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ 225,535,497,927 ብር፣


በአገር ውስጥ ከሚመረቱ ዕቃዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ 113,422,746,069 ብር፣


ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 3,639,722,663 ብር፣


ከስኳር 2,362,600,874 ብር መንግስተ ለመሰብሰብ ማቀዱን የ2019 በጀት ረቂቅ ሰነድ ያሳያል።



አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የ2019 ጠቅላላ ወጪ በጀት ብር 2.3 ትሪሊዮን ሲሆን፣ ይህም በ2018 በጀት ዓመት ከፀደቀው የወጪ በጀት አንጻር የብር 411.5 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ወይም የ21.3 በመቶ ዕድገት አለው፡፡


የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ወጪ እቅድን በተመለከተ ደግሞ ለመደበኛ ወጪ 1.2 ትሪሊዮን ብር ፣ለካፒታል ወጪ 568 ቢሊዮን ብር ተመድቧል፡፡


የካፒታል ወጪ በጀቱ ከመደበኛ በጀቱ በግማሽ ያንሳል፡፡


ከቀረበው ጠቅላላ የፌዴራል መንግስት የወጪ በጀት ውስጥ 52.9 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ ለመደበኛ በጀት የተመደበ ነው፡፡


ይህም በ2018 በጀት ዓመት ለመደበኛ በጀት ከተመደበው አንጻር የ16.5 በመቶ ዕድገት አለው።


ከዚህ ጠቅላላ የመደበኛ ወጪ ውስጥ ብር 542.1 ቢሊዮን ወይም 43.8 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ የተደለደለው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ ሲሆን፣ 236.4 ቢሊዮን ብር ወይንም 19.1 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለማዳበሪያና ለነዳጅ ድጎማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅትን ካፒታል ለማሳደግ የተመደበ በጀት እንደሆነ ሰነዱ አመላክቷል፡፡


520.6 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊና ክልላዊ መንግሥታት የበጀት ድጋፍ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የተመደበ በጀት እንደሆነ ተጠቅሷል


የቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የተጣራ የበጀት ጉድለት 308.6 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 5.7 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ እና 302.9 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ የተጣራ ብድር በመውሰድ እንዲሸፈን የታቀደ ነው፡፡


ይህም የተጣራ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 1.4 በመቶ እንደሆነ ያሳያል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 
በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡

ሰኔ 15/2018 በፀረ ተባይ ማምረቻና በሌሎችም ፋብሪካዎች መወገድ ሲኖርባቸው ከ2 እስከ 31 አመት ተከማችተው የሚገኙ አደገኛ ኬሚካሎች ክምችት መኖሩ ተነገረ ፡፡ የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ባካሄደው የክዋኔ ኦዲት በተለያዩ ሶስት ፋብሪካዎች ለአካባቢ ብክለት ምክንያት የሚሆኑ ከ69 ቶን በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page