መስከረም 7 2018 - የሴት አውሮፕላን አብራሪዎቼ ቁጥር 80 ደርሰዋል፤ ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Sep 17
- 1 min read
ከሴት አውሮፕላን አብራሪዎቼ በተጨማሪ በማኔጅመንት ደረጃ ያሉ የሴት ሰራተኞቼ ብዛትም ከሰባት መቶ አልፏል ብሏል አየር መንገዱ፡፡
በአየር መንገዱ ቴክኒሻንነት ሞያ እያገለገሉ ያሉ ሴቶች ቁጥርም 175 እንደሆም ሰምተናል፡፡
ተቋሙ በተለያዩ ደረጃዎች ሴቶችን አካትቶ መስራቱም እንደ አንድ ስኬት የሚያየው እንደሆነ ተናግሯል፡፡
በዚህም በተለያዩ ጊዜያት ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚደረጉ በረራዎችን አከናውኛለሁም ብሏል ተቋሙ፡፡

የአየር መንገዱ የሙሉ ሰዓት ሰራተኞቼ ቁጥርም ከ19,000 በልጠዋል ብሏል፡፡
አሁን በስራ ላይ ያሉ 145 አውሮፕላን አሉኝ ያለው አየር መንገዱ፤ በትዕዛዝ ላይ ሆነው በተለያየ ጊዜ ልረከባቸው የምጠባበቃቸው ደግሞ ከ100 በላይ ናቸው ሲል ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየጊዜው መዳረሻዎቼ እያሰፋሁ ነው ያለ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ 140 እንዲሁም በሀገር ውስጥ 23 መዳረሻዎች ደርሻለሁኝ ሲል ተናግሯል፡፡
ከሀገር ውስጥ መዳረሻቹ ዉስጥ በጸጥታ ችግር ምክንያት በረራ ያቆመባቸው የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች መኖራቸውም ተጠቁሟል፡፡
እኛ ይህንን የሰማነው የአየር መንገዱ ስትራተጂክ ፕላኒንግ ክፍል ስለ አየር መንገዱ እድገትና አሁን ያለበት ደረጃ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ዘርፍ ላሉ ባለሞያዎች ማብራሪያ በሰጠበት መድረክ ላይ ነው፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments