top of page

መስከረም 6 2018 - ኢትዮጵያ ህዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ትንባሆ ማጨስን የሚከለክል ህግ ስራ ላይ ብታውልም አፈጻጸሙ ግን የሚጠበቀውን ያህል አይደለም ተባለ

  • sheger1021fm
  • Sep 16
  • 1 min read

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከብዙ ሀገራት ምሳሌ ያደረጋትንና የዜጎቿን ጤና ለመጠበቅ ህዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ትንባሆ ማጨስን የሚከለክል ህግ ስራ ላይ ብታውልም አፈጻጸሙ ግን የሚጠበቀውን ያህል አይደለም ተባለ፡፡


ትምባሆ እና የትምባሆ ምርቶችን ማጨስን በተለይ በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም በነጠላ መሸጥን ህጉ ቢከለክልም ተከታትሎ ማስፈፀሙ ላይ ግን ክፍተቶች እንደሚታዩ ተነግሯል፡፡


ትምባሆ በጤና ላይ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ለማስቀረት የወጣውና ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የምትመሰገንበት ህግ በስራ ላይ ቢሆንም በነጠላ መሸጥ እና ሌሎች ተመሳሳይ ህጉን የሚጥሱ ድርጊቶች ግን አሁንም እንደሚታየዩ የሚናገሩት በጉዳዩ ላይ የሚሰራው የማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ መስራችና የበላይ የሆኑት አቶ ወልዱ በቀለ ናቸው፡፡


ከትምባሆ ምርቶች ጋር በተያያዘ ለመቆጣጠር በወጣው ህግ ቁጥጥር የተደረገ መሆኑን የሚናገሩት የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው እስካሁን በተሰሩት ስራዎች የሚቀጡ አካላት መኖራቸውን ነገር ግን ጉዳዩ ጠበቅ ያለ ቅጣት የሚጣልበትንና የወጣው ግን በአግባቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ያሉትን ክፍተቶች በመለየት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡


በተለያዩ የገበያ ቅኝቶች በተሰሩ ኦፕሬሽኖች ወደ 16.3 ሚሊዮን ብር በላይ የህገ ወጥ የትምባሆ ምርቶች ከገበያ ተሰብስቧል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ሺሻ ወደ ሃገር እንዳይገባ እገዳ ከተደረገባቸው የትምባሆ ምርቶች አንዱ ሆኖ በአዋጅ መሸጥም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ቢሆንም ምርቱን ወደ ሀገር በማስገባትና በመጠቀም የሚቀጡ አሉ አጠቃላይ የትምባሆ ምርቶች ቁጥጥርን በተመለከተ ያለው ህግ ጠበቅ እንዲል ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር አንዳንዶቹ የደምብ ጥሰቶች ወደ ወንጀል እንዲመጡ የአሠራር ማሻሻያዎች እየተደረገባቸው ነው ብለዋል፡፡


በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወጣው የትምባሆ ቁጥጥር በተጨማሪ አዲስ አበባ ላይ በከተማ ደረጃ የትምባሆ ቁጥጥሩን ለማጥበቅ እየሰተራ ነው የተጀመሩ ስራዎችም አሉ ተብሏል፡፡


የትምባሆ ምርትን መጠቀም ተከትሎ የሚመጣ የጤና ጉዳት ለመከላከል እንዲሁም ህክምናው ላይ ከተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን የማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ተናግሯል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…… https://www.mixcloud.com/ShegerFM/56u56/


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page