top of page

መስከረም 5 2018 - የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና   50 ት/ቤቶች በሙሉ ያስፈተኑትን ተማሪ ያሳለፉ ሲሆን፣ 1249 ት/ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

  • sheger1021fm
  • Sep 15, 2025
  • 1 min read

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና  ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል  8.4  ከመቶው  50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል፣ 1,249 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም ተብሏል።


በ2017 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛው 591 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።


በዚህ ወቅት 2,384 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለጋዜጠኛች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።


አዲስ አበባ 888 ተማሪዎች፣ ኦሮሚያ 794 ተማሪዎች፣ አማራ ክልል 385 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አምጥተዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን 585,000 ተማሪዎች የ12 ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን 8.4  ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ አምጥተዋል ተብሏል።


በ2016 ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ እንደነበሩ ይታወሳል።


የዘንድሮው ተፈተኞች ያመጡት አማካኝ ውጤት 31 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል።


አዳሪ ትምህርትቤቶች 87 ከመቶ ያስፈተኑትን ተማሪ ያሳለፉ ሲሆን ኮሚኒቲ ትምህርት ቤቶች ደግሞ 86 በመቶ አሳልፈዋል።


የመንግስት ትምህርት ቤቶች 5.6 በመቶ ተማሪ አሳልፈዋል።


በዚህ ዓመት 50 ትምህርት ቤቶች በሙሉ ያስፈተኑትን ተማሪ ያሳለፉ ሲሆን፣1249 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ በዚህ አመት አላሳለፉም።


የዘንድሮው ውጤት ካለፉት ዓመታት

የተሻለ ለመሆኑ የወላጆች ክትትል ከፍ ማለቱ ፣ የመምህራን አቅም ማሻሻያ ስልጠና መሰጠቱ አንዱ ምክንያት ነው ተብሏል።

 

የዘንድሮ የ12 ተኛ ክፍል ተፈተኞች አዲሱ የፈተና አሰጣጥ ሲጀመር የ9ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ ተማሪዎች ናቸው።


አሁን ተማሪዎች የፈተና ስርቆት እንደማያዋጣ አውቀዋል የምንፈልገው ለውጥ እየመጣ መሆኑን እየተመለከትን ነው ብለዋል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ።


የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ጣራ ከዚህ በኋላ እየጨመረ ይመጣል የሚል ግምት እንዳላቸውም አብራርተዋል።


የፈተናው ውጤት እስከ ነገ ከሰዓት ድረስ ይለቀቃል ተብሏል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page