top of page

መስከረም 15 2018 - የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተጨማሪ ሶስት የምርት ዓይነቶችን ወደ ግብይት ለማስገባት ዝግጅት ጨርሻለሁ አለ

  • sheger1021fm
  • Sep 25
  • 1 min read
ree

ምርት ገበያው ወደ ግብይት ሥርዓቱ ለማስገባት ተዘጋጅቻለሁ ያለው ጥጥ ፤ ኦፓል ፤ ቆዳና ሌጦን ነው።


ባለፈው ዓመት የቢራ ገብስ ፤ ጤፍ ፤ ተልባ ፤ የጎሎ ፍሬ ፤ ዳጉሳ እና ጎመን ዘር ወደ ዘመናዊ የግብይቱ ስርዓት መግባታቸውን ጠቅሷል።


አሁን ላይ የሚያገበያያቸው የምርት አይነቶች 28 መድረሳቸውም ተነግሯል።


በ2017 ሚያዝያ ወር ስራ ላይ ባዋለው የበይነ መረብ ወይም ኦንላይን ግብይት ከ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ከ27 ሺህ 830 ቶን በላይ ምርቶች እንዳገበያየም ሠምተናል።


ስራ ከጀመረ አስራ ሰባት ዓመት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የክፍያና የርክክብ ስርአትን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ ነው ተብሏል።


ምርት ገበያው ዛሬ 26ኛው የክፍያ አጋሩ ሆኖ እንዲሰራ ከሲዳማ ባንክ ጋር በዋና መስሪያ ቤቱ ስምምነት ተፈራርሟል።


በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ዘመናዊ ባለ 36 ወለል ህንፃ ምርት ገበያው እየገነባ እንደሚገኝም በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሲነገር ሠምተናል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page