top of page

መስከረም 14 2018 - ዘላቂና ብቁ የሆነ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚቻለው አባል ሀገራት በትብብር መስራት ሲችሉ ብቻ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Sep 24
  • 1 min read
ree

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎትን ከፍ ወዳለ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት ለማሳደግ የሚያስችል መግባባት ላይ መድረሳቸውም ተወርቷል።


ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ አበራ ናቸው።


ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የአለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት 42ኛ ጉባኤ በካናዳ ሞንትሪያል እየተካሄደ ነው።


ዋና ዳይሬክተሩ በአባል ሀገራቱ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህንኑ የትብብር አስፈላጊነት የተመለከተ ሀሳብ አንስተዋል ተብሏል።


ከ80 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ቺካጎ ከተማ የአለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅትን ለመመስረት በተካሄደ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ መስራች በመሆን የተሳተፈችው ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር ታሪካዊ ቁርኝት ያላት እንደሆነች አንስተዋል።


ኢትዮጵያ ዛሬ ጠንካራ የሲቪል አቪዬሽን አሰራር ዘዴዎችን መዘርጋት የቻለች ሀገር መሆናን ማንሳታቸውን ከተቋሙ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።


ከጉባኤው በተጓዳኝ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በሀገራቱ መሀከል ቀደም ሲል የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ሲያካሄዱት የነበረውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከፍ ወዳለ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መድረሳቸውም ተወርቷል።


ቴዎድርስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page