መስከረም 13 2018 - የተገኙ 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጥያቄ ቀረበ።
- sheger1021fm
- Sep 23
- 1 min read
የመንግስትን ጥቅም ለማሳጣት የሚያስችል ግድፈት ፈፅመው የተገኙ 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጥያቄ ቀረበ።
ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ነው።
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የ13 ግብር ከፋዮች መዝገብ በማዘጋጀት ካቀረቡ ባለሙያዎች መካከል ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የመንግስትን ጥቅም ለማሳጣት የሚያስችል ግድፈት ፈፅመው ተገኝተዋል በተባሉ 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች ላይ ነው የሙያ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ጥያቄ የቀረበው ተብሏል።

ቢሮው ይኸን ጥያቄውን ያቀረበው በታክስ አስተደደር አዋጅ መሰረት ለኢትዮጲያ የሂሳብና ኦዲት ቦርድ መሆኑ ተነግሯል።
በቢሮው የሙያ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ጥያቄ የቀረበባቸው 10 የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች በቦርዱ የሙያ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆናቸውንም አሳውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ግብር ከፋዮች ቢሮው የሙያ ፈቃድ ስረዛ በተጠየቀባቸው የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የሂሳብ መዝገቦችን አልቀበልም ብሏል።
የስም ዝርዝራቸውን ከቦርዱ በመጠየቅ የሙያ ስነ ምግባሩን ጠብቀው በሚሰሩ የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የሂሳብ መዝገቡን በማሰራት እንዲያቀርብ አሳስቧል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments