top of page

ሐምሌ 9 2017 - በሚሰጣቸው ትዕዛዝ የትኛውንም ስራ ሰርተው የሚመለሱ ሰው አልባ በራሪ አካላት(ድሮኖች) እንዳሉት የፌደራል ፖሊስ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jul 16
  • 1 min read
ree

ኮሚሽኑ ሁሉንም የሚበሩ ድሮኖች ከአንድ ማዕከል መቆጣጠር የሚያስችለኝን ቴክኖሎጂ ታጥቂያለሁ ብሏል፡፡


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተለያዩ ስራዎቹ የድሮን ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ መሆኑን ነግሮናል፡፡


ለእነዚህ ሰው አልባ በራሪ አካላት ለእያንዳንዳቸው ከዚህ ቀደም በሚሰማሩበትስፍራ ሁሉ የሚያበራቸው፤ስራቸውን የሚቆጣጠር ባለሙያ ይመደብላቸው ነበር አሁን ግን ኮሚሽኑ እየተጠቀምኩበት ነው ባለው ቴክኖሎጂ በየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ በተመሳሳይ ሰዓት ቢበሩ አንድ ማዕከል ላይ ባለ አንድ ባለሙያ መቆጣጠር ተችሏል ያሉን በፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር አለሙ ተሰማ ናቸው፡፡


ፖሊስ ኮሚሽኑ ድሮኖችን የሚጠቀመው በሰው አቅም መሰራት ከበድ ለሚሉ የምርመራና የአሰሳ ስራዎች ነው ያሉን ኢንስፔክተሩ እንደየስራው ሁኔታ ለእያንዳንዱን ድሮን ባለሙያዎች ሊመደብ ይችላል ብለውናል፡፡


ለመሆኑ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ድሮኖችን ለማብረር የምትጠቀሙበት ቴክኖሎጂ እንዴት ነው የሚሰራው ያልናቸው ሃላፊው ለፖሊስ በሚሰጠው የስምሪት ትዕዛዝ መሰረት ስራው የት መቼና እንዴት እንደሚሰራ እቅድ በማውጣት ለእያንዳንዱ ድሮን በስንት ሰዓት የት ደርሰው ምን ሰርተው እንደሚመለሱ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል በትዕዛዙ መሰረት ስራቸውን ሰርተው እንዲመለሱ ያስቻለ ቴክኖሎጂ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


በስራ ላይ ያለው ቴክኖሎጂ ፖሊስ ለሚሰማራባቸው የአሰሳ ተግባራት በተለይም በሃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት፣እጀባ የሚፈልጉ ትልልቅ ጉባኤዎች በሚካሄዱበት ወቅት ጥቅም ላይ እንደሚውል ከሃላፊው ሰምተናል፡፡


ምንታምር ፀጋው


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page