top of page

ሐምሌ 30 2017 - የሰዎች በሕይወት የመኖር መብት በአሳሳቢ ሁኔታ ጥሰት እየተፈፀመበት የቀጠለ የመብት ዓይነት መሆኑ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 6
  • 2 min read

የሰዎች በሕይወት የመኖር መብት በአሳሳቢ ሁኔታ ጥሰት እየተፈፀመበት የቀጠለ የመብት ዓይነት መሆኑ ተነገረ፡፡


በመንግስት ሀይሎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ በታጠቁ ቡድኖች፣ እንዲሁም ባልታወቁ ሰዎች ጭምር በ2017 ዓ.ም ቁጥራቸው የታወቁ በድምሩ ከ508 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡


ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በሚል የተገለፁ ብዙ ሰዎችም እንደተገደሉ ሰምተናል፡፡


ኢትዮጵያውያን በእርስ በርስ ግጭቶችን በታጠቁ ቡድኖች ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ደቡብ ሱዳንም በመጡ ታጣቂዎች በህይወት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ወድቆ እየተገደሉ መቀጠላቸው አሳሳቢ መሆኑን መንግስታዊው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል፡፡

ree

በተለይ የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልሎች የሰዎች በሕይወት የመኖር መብት አደጋ ውስጥ የገባባቸው ተብለው ተጠቅሰዋል፡፡


በደቡብ ኢትዮጵያና አፋር ክልልም ግን በተለያዩ ግጭቶች ሰላማዊ ሰዎች መገደላው በኢሰመኮ ዓመታዊ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡


ከመካከላቸው በአማራ ክልል ብቻ በተለያዩ ቦታዎች ቁጥራቸው በግልፅ ያልታወቀ ሰዎች መገደላቸው የተነገረ ሲሆን በቁጥር የታወቁ ንጹሃን 169 ሰዎች ባለፈው አንድ አመት መገደላቸውን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ተናግሯል፡፡


ከተገደሉት ብዙዎቹ በትጥቅ ግጭት መካከል በተባራሪ ጥይትና ኢላማውን በሳተ መሳሪያ ከቤታቸው እያሉ ጭምር የተገደሉ ናቸው፡፡


በሌላ በኩል በክልሉ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ፋኖ የተሰኘ ሀይል እና የመንግስት ሀይሎችም ሆን ብለው እና በበቀል ስሜት የገደሏቸው ሰላማዊ ሰዎችም እንዳሉ የኢሰመኮ ሪፖርት ያሳያል፡፡


በክልሉ ተገደሉ ተብለው ከተጠቀሱት ንጹሃን መካከል ህፃነትና ሴቶችም ይገኙበታል፡፡


በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ቤታቸው የተቃጠለባቸው አሉ የተባለ ሲሆን የአካል ጉዳትና የተለያዩ የንብረት ውድመትም በክልሉ መስተናገዱን ኢሰመኮ ተናግሯል፡፡


በሌላ በኩል በቤኒሻነጉል ጉሙዝ ክልልም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እና በኦነግ ሸኔ በድምሩ 25 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል፡፡


ከመካከላቸው በወርቅ ማውጫ ማዕድን ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ የመንግስት ሀይሎች እንደሚገኙበትም ተጠቅሷል፡፡፡


በ2017 ዓመት በማዕከላዊ ኢትዮጵያም ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡


በጋምቤላ ክልል ደግሞ ከተገደሉ ንጹሃን ሰዎች መካከልም፤ በክልሉ የተጠለሉ ስደተኞችም እንደሚገኙበት ሰምተናል፡፡


በኦሮሚያ ክልልም በተያዘው ዓመት ብቻ በቀጠለው ወታደራዊ ግጭት በርካታ ንጹሃን መገደላቸውንና ከ540 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ኢሰመኮ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡


የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም በርካቶች ሲሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤታቸው ተቃጥሏል፣ ትራክተርና የመሳሰሉ ቁሶችም በእሳት እንዲወድሙ ተደርጓል ተብሏል፡፡


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም 34 ንጹኃን ሰዎች መገደላቸው የተነገረ ሲሆን በድምሩ በተለያዩ ክልሎች በ2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር ብቻ ከ500 በላይ ንጹሃን መገደላቸው ኢሰመኮ ተናግሯል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page