top of page

ሐምሌ 19 2017 - አቢሲኒያ ባንክ ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ በሆነ መልኩ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመርኩ አለ።

  • sheger1021fm
  • Jul 26
  • 1 min read

ይህ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት ዘመናዊ የባንክ አሠራሮችን እንዲይዝ ተደርጎ በአዲስ መልክ በባንኩ ራስ ልዩ ቅርንጫፍ (Ras Premium Branch) በዛሬው ዕለት በተከናወነ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል።


በዚህ አዲስ አሠራር ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ያስችለኛል ያለው #አቢሲኒያ_ባንክ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ጥሬ ገንዘብ ማስገባትና ማውጣት፣ ሒሳብ መክፈትና ሌሎች ከቅርንጫፍ አገልግሎት ጋር የተገናኙ ማናቸውንም አገልግሎቶች ደንበኞች ራሳቸው ወይም በባንኩ ሠራተኞች በመታገዝ መጠቀም ይቻላሉ ብሏል።


አገልግሎቱ የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀም መሆኑ የተነገረ ሲሆን ጊዜ የሚወስዱ የአሠራር ሂደቶችን ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ree
ree

ይህን አዲስ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ ባሉ በሁሉም ቅርንጫፎች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።


አገልግሎቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራዊ የቋንቋ አማራጮች ማለትም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በሱማሌኛ፣ በትግርኛ፣ በአፋርኛ እና በሲዳምኛ የቀረበ እንደሆነ ተናግሯል።


የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ግለሰቦች በቅርንጫፍ ውስጥ ወረፋ መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው የጥሬ ገንዘብ መቀበያና መክፈያ (Recyclers) እና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብን ለመቀበል የሚያስችሉ ማሽኖች (Bulk Deposit Machines) በተመረጡ ቅርንጫፎች ማዘጋጀቴን እወቁልኝ ብሏል ባንኩ፡፡


የአቢሲኒያ ባንክ ይህ አሰራት ወደፊት በሁሉም ቅርንጫፎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ፤ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ በቃሉ ዘለቀ አስረድተዋል፡፡


በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ፤ አቢሲኒያ ባንክ ይህንን ቴክኖሎጂ ማስጀመሩ የሚበረታታ ነው ብለዋል።


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page