ሐምሌ 16 2017 - ከ10 ዓመት በፊት 1.7 ቢሊየን ዶላር የተመደበለት የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ጉዳቱ ተጠንቶ ተለይቷል ተባለ
- sheger1021fm
- Jul 23
- 1 min read
ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ ጋር ያገናኛል የተባለው በቱርኩ ያፒ መርከዚ ተቋራጭ ከ10 ዓመት በፊት 1.7 ቢሊየን ዶላር የተመደበለት የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ጉዳቱ ተጠንቶ ተለይቷል ተባለ።
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈፅሞበታል የተባለው፤ ስራውም ተቋርጦ የቆየው ይህ ፕሮጀክት እንደገና ለመቀጠልም ስራ መጀመሩ ተሰምቷል።
ባቡሩ ከጦርነት እና ግጭት ባለፈ በተፈጥሮ፤ መሬት መንቀጥቀጥ ጭምር የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ጉዳት እንደደረሰበት ተረድተናል።

የዚህን ፕሮጀክት ዳግም ጀምሮ ለማጠናቀቅ ጉዳቱ እንደተለየና በእቅድ እንደተያዘ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ህሊና በላቸው ነግረውናል።
አዋሽ ወልዲያ ሀራ ገበያ የባቡር ንጣፍ መስመር ፕሮጀክት 375 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው።
መስመሩ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያን ከማእከላዊ ኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝ ነው።
የአፋር፣ የአማራና የትግራይ ክልሎች ደግሞ ይኸው የባቡር ንጣፍ መስመር የሚያልፍባቸው ናቸው።
ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ ጋር ያገናኛል የተባለው ይህ ባቡር በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር እንዲወረወር ተደርጎ ዲዛይን የተደረገለት ነበር።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments