ሐምሌ 10 2017 - የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅና የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ፀደቀ
- sheger1021fm
- Jul 17
- 1 min read
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ እና የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ዛሬ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቦ ፀደቀ፡፡
ምክር ቤቱ 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ አድርጓል፡፡
በዛሬው ስብሰባውበኢትዮጵያ #የምርጫ_የፖለቲከ_ፓርቲዎች_ምዝገባና_የሥነ_ምግባር አዋጅን በማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የሚቀርቡ ሪፖርትና የውሳኔ ሀ ቦችን መርምሮ ለማፅደቅ ቀጠሮ ይዞ ነበር፡፡
በዚህ መሰረት ብዙ ክርክርና ሲደረግበት የነበረው #የገቢ_ግብር አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ በሁለት ተቃውሞና በ4 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
በ26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ ተደረገበት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ቁጥር 1394/2017 ሆኖ በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments