top of page

ሐምሌ 10 2017 - በአዲስ አበባ በክረምቱ ዝናብ ምክንያት ለጎርፍ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ 147 ቦታዎች ተለይተዋል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jul 17
  • 1 min read

አቃቂ ቃሊቲ የበለጠ ተጋላጭ ይሆናል ቢባልም ሁሉም ክፍለ ከተሞችም ግን የተለያየ ደረጃ ስጋት እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡


ይህን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።


ኮሚሽኑ ክረምቱን ተከትሎ ለሚከሰቱ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ ብሏል።


ክረምቱን ተከትሎ አደጋዎች እንዳይከሰቱም ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እና ጥንቃቄም እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ጥሪ አቀርቧል።

ree

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ም/ ኮሚሽነር ደሳለኝ ፉፋ በከተማዋ ዙሪያና በመሀል ጭምር ለአደጋ ተጋላጭ ቦታዎችን በአካል በማየት ቅድመ አደጋ መከላከል ወይም የአደጋ ቅነሳ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል።


የአየር ትንበያ መረጃን መሰረት በማድረግ በተለይ የአደጋ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ከቤት ለቤት እስከ ሚዲያ አውታሮችን ጭምር በመጠቀም የጥንቃቄ መልእክቶችን እያስተላለፍን ነውም ብለዋል።


ክረምቱን ተከትሎ አደጋዎች እንዳይፈጠሩ ህብረተሰቡ እራሱን መጠበቅ አለበት የሚሉት ም/ኮሚሽነሩ በኮሚሽኑ በኩል የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን መከታተል እና ወደ ተግባር ገብቶም አደጋዎች እንዳይከሰቱ ከኮሚሽኑ ጋር መተባበር እንደሚገባም አሳስበዋል።


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page