top of page

ነሐሴ 23፣2016 - በይፋ ወደ ስራ የገባው ካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ ተብሎ የሚጠራው አሰራር በዝርዝር ምንድነው?

  • sheger1021fm
  • Aug 29, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በገበያው ገብተው መሳተፍ የሚፈልጉ ተዋንያን የሚሰሩበትን ሁኔታ የሚፈትሸበት ሜዳ አለ።


ይህ መንገድ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተርና እና በቁጥጥር ማዕቀፍ የእድገት ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ተድርጎ ሊቆጠር የሚችል እና ትልቅ ጅምር መሆኑን ባለስልጣኑ ያምናል።


በመሆኑም የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ( #Regulatory_Sandbox ) ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተሰምቷል።


የቁጥጥር ማዕቀፍ ማጣርያው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ገበያ ያሻግራል ተብሏል።


የቁጥጥር ማጣርያ ማዕቀፉ የተቀረጸው የፋይናንስ ቴክኖሎጂዎችን (FinTechs)፣ አነስተኛ እና መካከለኛ #ኢንተርፕራይዞችን (SMEs) እና በሌሎች ኢንተርፕራይዞች የሚፈጠሩ አዳዲስ የካፒታል ገበያ ምርቶችን ለመፈተሽ ነው።


ይህ መንገድ ሌሎች አገልግሎቶችን እና የንግድ ሞዴሎችንም በባለስልጣኑ የቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው የሚሞከሩበት የስራ ከባቢ እንዲኖር ያደርጋል።


#የኢትዮጵያ_ካፒታል_ገበያ የቁጥጥር ማጣርያ ማዕቀፍ አዳዲስ ስራ ፈጣሪዎች፣ በስራ ያሉትን የቁጥጥር ደንቦችንና መመሪያዎችን መከተል ሳይጠበቅባቸው አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎቶቻቸውን እንዲሞክሩ የተዋቀረ ቁጥጥር የሚደረግበት የሙከራ ሜዳ ነው።


ይህ ልዩ ማዕቀፍ ተቆጣጣሪ ተቋማትም ሆኑ ፈጣሪዎች የአዳዲስ የፋይናንስ ምርቶች እና አገልግሎቶችን ተፅዕኖ፣ ደህንነት እና ውጤታማነት በተጨባጭና ግልፅ በሆኑ መለኪያዎች ውስጥ በማለፍ ለገበያው የማይስማሙ ችግሮችን በመለየት የተሻለውን ለመገምገም ያስችላቸዋል።


ለመሆኑ ዛሬ በይፋ ወደ ስራ የገባው ካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ(Regulatory Sandbox) ተብሎ የሚጠራው አሰራር በዝርዝር ምንድነው?


ተህቦ ንጉሴ

コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page