የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አዳዲስ መሪ ተሾመላቸው።
ላለፋት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣንን ሲመሩ የቆዩት ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) ከነበሩበት የሀላፊነት ቦታ ተነስተዋል።
በምትካቸውም ሀና ተኸልቁ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣንን እንዲመሩ ተሹመዋል።

ብሩክ ታዬ(ዶ/ር)

ሀና ተኸልቁ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሲመሩ የቆዩት አብዱራህማን ኢድታሂርም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ተነግሯል።
ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መሪነት የተነሱት ብሩክ ታዬ(ዶ/ር)፤ አብዱራህማን ኢድታሂርንን ተክተው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግን እንዲመሩ ተሹመዋል ተብሏል
ማንያዘዋል ጌታሁን
Comments