መስከረም 29፣2017 - የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና ብሔራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ትግበራን በጋራ ሊሰሩ ነው
- sheger1021fm
- Oct 9, 2024
- 1 min read
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ትግበራን በጋራ ሊሰሩ ነው።
በኤጀንሲው በሁሉም ወረዳዎች እና ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በዋና መስሪያ ቤት እና በሁለቱ ቅርንጫፎች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባው ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል።
ጉዳዩን አስመልክቶም ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራታቸው በከተማ ደረጃ የሚከወነውን የፋይዳን የዲጅታል መታወቂያ የምዝገባ ስራ ያፋጣጥናል ተብሎ ታምኖበታል።
ሀሰተኛ ሰነድ መበራከት እና ሌሎች ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመቀነስ ያግዛል የተባለለት ይሄው መታወቂያ ከነገ ጀምሮ ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ በየወረዳው እና በየክፍለ ከተማው በመሄድ ተመዝግቦ የፋይዳ መታወቂያውን መውሰድ ይቻላል ተብሏል።

የንግድ ፍቃድ ለማውጣት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ መኖር አስፈላጊ ነው የተባለ ሲሆን ከዚህ በኋላም በባንክ እና ለሌሎች አገልግሎታችን ለመጠቀም መታወቂያው አስፈላጊ እንደሆነ ተነግሯል።
ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ባዮሜትሪክ እና አሻራ በመሰብሰብ አንድን ሰው መለየት የሚያስችል እና ለሁሉም አገልግሎት ሰጭዎች በኤሌክትሮኒክ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማወቅ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው ተብሎለታል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments