top of page

ጥር 6፣ 2015የብራዚሉ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጂየር ቦልሶናሮ አመፅ በማነሳሳት ምርመራ ሊካሄድባቸው ነው


የብራዚሉ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጂየር ቦልሶናሮ አመፅ በማነሳሳት ምርመራ ሊካሄድባቸው ነው፡፡


ቦልሶናሮ ምርመራ የሚካሄድባቸው ባለፈው ሳምንት እሁድ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው በርዕሰ ከተማዋ ብራዚሊያ ፓርላማው ፣ ቤተ መንግስቱን እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕንፃዎች በወረሩበት ድርጊት እንደሆነ SBS ፅፏል፡፡


የቀድሞው ፕሬዝዳንት በጥቅምት ወር በተካሄደው ዳግም ምርጫ በግራ ክንፈኛው ሉላ ኢናሲዮ ዴ ሲልቫ በጠባብ ልዩነት መሸነፋቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡


ቦልሶናሮ ግን ሉላ አልተመረጠም የሚል የቪዲዮ ምስል አሰናድተው እዩልኝ ብለው ነበር፡፡


ይህም ህጋዊውን ምርጫ ዋጋ ለማሳጣት የተደረገ የአመፅ ማነሳሻ ተደርጎ መቆጠሩ ተሰምቷል፡፡


ጂየር ቦልሶናሮ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ይገኛሉ፡፡


ምርመራው ሌሎችንም የቀድሞ ባለስልጣናት ጭምር ይመለከታል ተብሏል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page