የኩዌት መንግስት የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረበ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ አህመድ ናዋፍ የስልጣን መልቀቂያውን እንዳቀረቡ CGTN
ፅፏል፡፡
ካቢኔው የስልጣን መልቀቂያውን ያቀረበው ተቃዋሚዎች ከሚልቁበት ፓርላማ ጋር ባለመግባባቱ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡
የመንግስት የስልጣን መልቀቂያ ማቅረብ በአገሪቱ አጣዳፊ የፓርላማ ምርጫ እንዲካሄድ የሚያስገድድ እንደሆነ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የስልጣን መልቀቂያ ያቀረበው ካቢኔ ሀላፊነቱን የተረከበው በጥቅምት ወር ነበር፡፡
በኩዌት ተሰናባቹ ካቢኔ በ3 ዓመታት ጊዜ 6ኛው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
በኩዌት ቀጥሎ የሚካሄደው የፓርላማ ምርጫ በ3 ዓመታት 7ኛው ይሆናል ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments