top of page

የካቲት 30፣2016 - የካፒታል ገበያ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎችን ለመደገፍ፣ መንገዱን ለማሳየት ሁለት ተቋማት የትብብር ስምምነት አደረጉ

በቅርብ ጊዜ ስራው ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የካፒታል ገበያ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎችን ለመደገፍ፣ መንገዱን ለማሳየት ሁለት ተቋማት የትብብር ስምምነት አደረጉ፡፡


ተቋማቱ ኤም ኤል ኤ(MLA) የተባለው የህግ ቢሮ እና አክሲስ ካፒታል(Axis Capital) ናቸው፡፡


ከ25 ዓመታት በላይ በፕሮጀክት ፋይናንስ እና በድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ በድርጅት እና ግብይት ህግ ስራ ልምድ አለኝ ያለው የምህረተ አብ ልዑል የህግ ቢሮ(ኤም ኤል ኤ) ከአክሲስ ካፒታል ጋር ያሰረው የትብብር ስምምነት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ስራ ቀና እንዲሆን ያግዛል ተብሏል፡፡


የትብብር ስምምነቱ ዋና ዓላማም ወደ ካፒታል ገበያው መግባት ለሚፈልጉ ኩባንያዎችን መንገዱን ማሳየት ነው ተብሏል፡፡


ንጋቱ ሙሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page