top of page

የካቲት 28፣2016 - በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተበራክተዋል ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተናግሯል

በለንደን የሚገኘዉ የኤርትራ ኤምባሲ ባለፈው ያወጣው መግለጫ፤ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ክልል እንደሚገኝ ያረጋገጠ ነዉ ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተናግሯል።


በለንደን የኤርትራ ኤምባሲ፤ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት እንደሌሉ ተነግሮ አሁን የያዛቸው ቦታዎችም የኢትዮጵያ ሳይሆን ሕውሃት ከ20 ዓመት ባላይ በሃይል ይዞት የቆየው የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት መሆኑን አስረድቶ ነበር፡፡


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ፤ የኤምባሲው መግለጫ የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ እንደሌለ ሳይሆን መኖሩን ያረጋገጠ ነዉ ሲል ተናግሯል።


በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም ተበራክተዋል ሲሉ የነገሩን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ረዳይ ሃለፎም ናቸዉ።


ሃላፊው በኤርትራ ሰራዊት የተያዙ አካባቢዎች ማለትም የኩናማ እና የኢሮብ ማህበረሰብም የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል።


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


bottom of page