top of page

ታህሳስ 6፣ 2015- የቱርኩ ሰው አልባ በራሪ አካል አምራች እና አቅራቢ ባያካር ኩባንያ ከድምፅ የፈጠነ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ መሞከሩ


የቱርኩ ሰው አልባ በራሪ አካል አምራች እና አቅራቢ ባያካር ኩባንያ ከድምፅ የፈጠነ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ መሞከሩ ተሰማ፡፡


ኩባንያው ቀደም ሲል ባይራክታር ሰው አልባ አጥቂ ድሮኖችን ሲያመርት እና ሲያቀርብ መቆየቱን ኒውስ ዊክ ፅፏል፡፡


ከድምፅ የፈጠነውን አዲሱ ስሪቱን ድሮን ኪዚሌልማ የሚል ስያሜ ሰጥቶታል፡፡


ባያካር ኩባንያ ለዩክሬይን ባይራክተር ድሮኖችን እያቀረበ መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡


ኩባንያው አዲስ ስሪቱን ከድምፅ የፈጠነ ድሮን ለገበያ ለማቅረብ የሚያዘገየኝ አንዳችም ምክንያት የለም ማለቱ ተሰምቷል፡፡


የባያካር የስራ ሀላፊዎች ከድምፅ የፈጠነውን ድሮን የልብ አድርስ እና አንጀት አርስ ሲሉ መጥራታቸው ተሰምቷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


bottom of page