top of page

ታህሳስ 26፣2016 - የህብረት ስራ ማህበራት በርካታ ውስብስብ ችግሮችም አሉባቸው ተባለ

የህብረት ስራ ማህበራት ገበያን በማረጋጋት በኩል የእራሳቸው ሚና እየተጫወቱ ቢሆንም በርካታ ውስብስብ ችግሮችም አሉባቸው ተባለ።


የብቃትና ተወዳዳሪነት ማነስ፣ የሃብት ብክነትና ዘረፋ እንዲሁም የፋይናንስ እጥረት ከችግሮቹ መካከል እንደሆኑ ተነግሯል።


የቅንጅት ችግርና የአመራር ብቃት ማነስም በኢትዮጵያ የህብረት ስራ ማህበራት ላይ ይታያሉ የተባሉ ሌሎች ችግሮች ናቸው።


አነዚህን እና መሠል የማህበራቱን ችግሮች ለመፍታት ዘርፉን ሪፎርም ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

የእዚሁ ሪፎርም የማብሰሪያ መርሃ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።


ሪፎርሙ የህብረት ስራ ማህበራቱ ጠንካራ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ያስችላል የተባለ ሲሆን አመራራቸውንም የሚያጠናክር እንደሚሆን ተመልክቷል።


የገበያ ድርሻቸውን እና ተፅዕኗቸውን እንደሚያሳድግም በመርሃ ግብሩ ላይ ሲነገር ሠምተናል።

የፋይናንስ ችግራቸውን ለመፍታት የህብረት ስራ ባንክ እንደሚቋቋም ተነግሯል።


በሂደት ደግሞ አገር አቀፍ የህብረት ስራ ሊግ እንደሚያደራጅ ነው የተጠቀሰው።


አሁን ላይ በኢትዮጵያ 110 ሺህ መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት፣ 403 ፌዴሬሽኖች እና 5 ዩኒየኖች እንዳሉ ሠምተናል፡፡


28.5 ሚሊየን ግለሰብ አባላት ያሏቸው እነዚህ መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት አጠቃላይ ካፒታላቸው 49 ቢሊየን ብር እንደሆነ ተነግሯል።


በማብሰሪያ መርሃ ግብሩ የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡


ንጋቱ ረጋሳ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2024 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page