አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ነብይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ደራሲ ነብይ መኮንን ባደረበት ህመም ምክያት በመኖሪያ ቤቱ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ህይወቱ ማለፋን ሸገር ከልጁ ራዕይ ነብይ ሰምቷል።
ደራሲ እና ወግ አዋቂው ነብይ ህይወቱ ያለፈው በተወለደ በ68 ዓመቱ ነው።
ነብይ መኮንን ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ መሥራቾች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ጋዜጣዋን በዋና አዘጋጅነት መምራቱን የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

የሶስት ሴት ልጆች አባት የሆነው የነብይ መኮንን የቀብር ስርዓት፤ ባለቤቱ እና ልጁ ከውጭ ሀገር ከመጡ ብኋላ እንደሚፈፀም ልጁ ራዕይ ነግራናለች።
"ነገም ሌላ ቀን ነው" የትርጉም ስራ፣ ተከታታይ የግጥም መድብሎች፣ የጉዞ ማስታወሻዎች እንዲሁም የተውኔት ስራዎችን ደራሲ ነብይ መኮንን አሳትሞ ለንባብ አብቅቷል።
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በደራሲ ነብይ መኮንን ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል።
ለቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹም መፅናናትን ይመኛል።
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments