top of page

መጋቢት 29 2017 - የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከመሀል ሀገር ጀምሮ ሀዲዱ እስከተነጠፈበት ጅቡቲ ድረስ ፍጥነቴን ልጨምር መሆኑን እወቁት አለ

  • sheger1021fm
  • Apr 7
  • 1 min read

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከመሀል ሀገር ጀምሮ ሀዲዱ እስከተነጠፈበት ጅቡቲ ድረስ ፍጥነቴን ልጨምር መሆኑን እወቁት አለ።


ምድር ባቡሩ በሰአት 80 ኪሎ ሜትር መወርወሬ አይቀርም ብሏል።


በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ 50 በመቶውን ገቢና ወጪ እቃ በዚሁ መስመር አቀላጥፈዋለሁ ያለው ምድር ባቡር ለዚህም ፍጥነቴን በሰአት 80 ኪሎ ሜትር አደርጋለሁ ብሏል።


በተደጋጋሚ በእንስሳት ግጭት እና ካሳ ሰበብ ጭነት የያዙ ባቡሮች እየታገቱ መቆየታቸው ምድር ባበቡሩን ሲፈትነው ቆይቷል።


ይህንና ሌሎች ፈተናዎችን አሻሽዬ የሀገሪቱን ገቢ ወጪ ንግድ 50 በመቶ በዚሁ ለማድረግ አቅጃለሁ ብሏል።


ኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከዚህ በተጨማሪም የመንገደኛ መጓጓዣው ንፅህና ተጠብቆ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግሯል።


ሙሉ ዘገባውን….


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page