ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ያስመዘገቡ አራት ኩባንያዎች የማዕድን ማምረት ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡
የፈቃድ ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኘ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስፈጻሚዎች ተፈራርመዋል፡፡
ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሮሚን፣ የግራናይት፣ የድንጋይ ከሰል እና የደለል ወርቅ ማእድናትን ለማልማት በተወሰነው ስምምነት መሰረት ነው ሲል የማዕድን ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ኩባንያዎቹ የማዕድን ምርመራ ፈቃድ ወስደው የምርመራ ስራ በመስራት እና ከእዚህ በፊት የተሰሩ ጥናቶችን መረጃ በመጠቀም ወደ ምርት ለመግባት የሚያስችል የቴክኒክና የፋይናስን መረጃዎችን አሟልተው በመገኘታቸው ነው መመረጣቸውም ተነግሯል፡፡
የማምረት ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች ጄሬህ ኬሚካል ኢንዱስትሪያል ኃ/የተ/ የግል/ማህበር፣ ራፊቅ ሁስኒ ፋሪስአልቀብ፣ ሰኮያ ማይኒንግ እና ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/ የግል/ማህበር እንዲሁም ኦሮሚያ ማይኒግ አ/ማህበር መሆናቸው ተነግሯል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios