ይህን አሰራር ወደ ሥራ ለማስገባት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትና ኢትዮ ቴሌኮም አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል።
ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም ከንግድና ተጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር የነዳጅ አቅርቦት የአሰራር ስርዓትን እና የነዳጅ ኩፖንን ዲጂታል ለማድረግ የሚያስችል አገልግሎትን ይፋ አድርገዋል።
በተጨማሪም የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለትን በተቀናጀ የዲጂታል ሥርዓት ለማከናወን የሚያስችል የነዳጅ አቅርቦት ትስስር አስተዳደር መፍትሄ ወይም (Fuel Supply Chain Management System) በማበልጸግ ወደ ሥራ መግባቱን ሰምተናል፡፡
ይህ መፍትሄ በነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ ልማዳዊ የአሰራር ሂደቶችን ያስቀራል ተብሏል።
በወረቀት ላይ የተመሰረቱ አሰራሮችን ለማዘመን፣ ግልጽነት ያለው የነዳጅ አቅርቦትና ግብይትን ለማስፈን እንደሚያግዝ የሥራ ሀላፊዎቹ ተናግረዋል።
ትክክለኛ መረጃ በወቅቱ ለማግኘትና በሂደቱ ውስጥ ለሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ግዢ የሚውል የውጪ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ ትልቅ ግልግል ነው ተብሏል፡፡
ዲጂታል አሰራሩ የነዳጅ ጣቢያዎችና ቀጥተኛ ደንበኞች፣ የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች፣ የኢትዮጵያ የፔትሮሊየም አቅራቢ ድርጅት እንዲሁም የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አጠቃላይ የነዳጅ አቅርቦት መስመር ላይ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል ያስችላል ተብሏል።
የነዳጅ አቅርቦት ትዕዛዝን በዲጂታል ለመስጠት ለማቅረብ፣ ትዕዛዝ ለመቀበል እንዲሁም አስፈላጊውን ዳታ በወቅቱ ለማግኘት በብርቱ እንደሚያግዝም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም የማንዋል የነዳጅ ኩፖን ሽያጭ አገልግሎት አስራርን ወደ ወረቀት አልባ የዲጂታል ኩፖን በመቀየር አዲሰ አሰራር አስተዋውቋል።
ይህ ዘመናዊ አሰራር የነዳጅ ኩባንያዎች የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የነዳጅ ማደያዎችን የአገልግሎት አማራጭ ያሳድጋል ተብሏል።
በተጨማሪም የገንዘብ ፍሰትን ለማሻሻል፤ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የተጠቃሚዎችን መጠን ለመጨመር እና ሽያጭ ለማሳደግ፤ የዲጂታል ኩፖን ዳታዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ ግብይት ለማካሄድ የሚያስችል የዲጂታል ሶሉሽን ነው።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments