ሰኔ 26፣2015
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር የሱዳኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ ግጭቱ እንደሚነሳ ያውቁት ነበር ተባለ፡፡
የሱዳኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ግጭቱ አይቀሬ ስለመሆኑ በደህንነት አማካሪያቸው ቱት ጋትሉአክ ነግረዋቸው እንደነበር ሱዳንስ ፖርት ፅፏል፡፡
ጋትሉአክ ለሳልቫ ኪር እንደነገሯቸው ጦርነቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ መቀስቀሱ በዘባው ተጠቅሷል፡፡
ስለ ጉዳዩ ከደህንነት አማካሪያቸው እንደሰሙ ሳልቫ ኪር የቤተሰብ አባሎቻቸው ከሱዳኗ ርዕሰ ከተማ ካርቱም እንዲወጡ አድርገዋል ተብሏል፡፡
የሱዳን መንግስት ጦር እና RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በውጊያ ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Commentaires