በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት 16,933 ጥንዶች ተጋብተናል፤ 2,813 ጥንዶች ደግሞ ተፋትተናል ብለው ተመዝግበዋል ተባለ።
አግብተናል ብለው ከተመዘገቡት 16,933 ጥንዶች ውስጥ አዲስ ጎጆ ወጪ የሆኑት 5,171 ጥንዶች ናቸው ሲል የከተማዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተናግሯል።
የጋብቻ የምስክር ወረቀት ከወሰዱት ተጋቢዎች ውስጥ 72.8 ከመቶ የሚሆነው ተገቢ እድሜያቸው ከ18 -40 ዓመት ሲሆን ሲሆን 27.2 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ እድሜያቸው ከ41 በላይ መሆኑ ትንተናው አሳይቷል።
በ2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት አፈፃፀም ከባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ቁጥር የላቀ የኩነት እና የዲጂታል ምዘገባ ተከናውኗል ተብሏል።
በአዲስ አበባ ከ393 ሺህ በላይ የዲጂታል ምዝገባ እና ከ210 ሺህ በላይ የኩነት ምዘገባ መደረጉን ኤጀንሲው አስረድቷል።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በሲቪል ምዝገባ ዘርፍ ከ210 ሺህ በላይ ኩነት የተመዘገበ ሲሆን ከጠቅላላ ኩነት ምዘገባ እቅድ አንፃር ሲታይ ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል ተብሏል።
በጊዜ ማዕቀፉ 29,033 ህፃናት የልደት ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ይህም በ70 ጤና ተቋማት ላይ እየተተገበረ ያለው የምዝገባ ስርዓት የልደት ምዝገባ ሽፋን ላይ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተጠቅሷል።
በስድስት ወሩ ውስጥ ለ393,303 ነዋሪዎች አዲስ፣ ምትክ፣ እርማት እና በእድሳት የመታወቂያ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 311, 446 (93%) የዲጂታል መታወቂያ መሆኑ ተነግሯል።
በተጨማሪም 76,299 ሰዎች ላጤ ነን ብለው የያላገባ ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments